ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ፡ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ፡ ዳልቦ አጥዋሮ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Send-a-Cow-Reportertenders-1

Overview

 • Category : Water Proof Work
 • Posted Date : 12/28/2022
 • Phone Number : 0461804011
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/11/2023

Description

 ለምንጭ ማጎልበት የወጣ የጨረታ ማሰታወቂያ

ድርጀታችን ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎችና  ዞኖች በርካታ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ድርጅታችን በወላይታ ዞን ፡ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ፡ ዳልቦ አጥዋሮ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ተጫራቾች መሳተፍ እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡

 1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2015 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
 3. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/TIN NUMBER/ያለቸው፡፡
 4. ተጫራቾች GC ደረጃ 6 ወይንም WWC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ፡፡
 5. የጨረታዉን ማሰከበሪያ (CPO) 10,000/አስር ሺህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለዉ ከዚህ ቀደም በሶስት ባለፉት ዓመታት የሰሩበትን ሶስትና ከዚያ በላይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 7. ከዚህ በፍት ስራዉን አጠናቅቆ ርክብክብ ያደረጉበትን ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ ጊዜያዊና መጨረሻ የርክብክብ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የሪተንሽንና መጨረሻ ዙር ክፍያ ሰነድ።
 8. ተጨማሪ ለግምገማ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች (የታደሰ የሙያ ፍቃድ — ወዘተ)
 9. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናዉንና ኮፒዉን በሰም በታሸገ እንቭሎፕ ማቅረብ አለባቸዉ፡
 10. የጨረታ ማስገቢያው ማክሰኞ ጥር 02/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 የሚያበቃ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
 11. የጨረታዉ አሸናፊ ከተገለፀ በኃላ አሸናፊው ተጫራች በ2/ሁለት/ ቀናት ዉሰጥ በአካል በመቅረብ ዉል መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታዉ ያስያዙት የጨረታ ማሰከበሪያ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 12. ተጫራቾች የመስክ/ሳይት ምልከታ ማድረግና ከቀበሌው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 13. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት እስክ ጥር 02/2015 ዓ.ም ብቻ አየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 14. ማሳሰቢያ፡ የጨረታ ሰነዱን ወላይታ ሶዶ ሉትራን/አሜርካን ኢንተርናሽናል አካዳሚ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው የሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በስራ ቀንና ሰአት በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡ የጨረታ ሰንድ ማስገቢያው ስፍራውም በዚሁ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461804011/0461804463 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡