ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ የእንሰሳት መኖ ዘር እና የሳር ግንጣዮችን በዘርፉ ልምድና ተገቢው ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

Send-a-Cow-Reportertenders

Overview

 • Category : Flora & Horticulture
 • Posted Date : 07/09/2021
 • Phone Number : 0116477233
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/21/2021

Description

                                                               እንሰሳት መኖ ዘርና ሳር ግንጣይ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ በደቡብ ብሔር፡ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፣በወላይታ ዞን በሚገኙ 3 ወረዳዎች እየተገበረ ላለው ፕሮጀክት ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን ለማገዝ የተለያዩ ጥራታቸው የተጠበቀና የተሻሻሉ የእንሰሳት መኖ ዘር እና የሳር ግንጣዮችን በዘርፉ ልምድና ተገቢው ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ድረጅታችን  በዘርፉ የተሰማራችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩተን የዘርና የሳር ግንጣይ ዓይነቶችን  ለማቅረብ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

ተ/ቁ

የዘሩና የግንጣዩ ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

 ምርመራ

1.        

ሙላቶ 2 (ብራካሪያ ሳር ዝርያ)

ግንጣይ

145 000

በበሽታና በተባይ ያልተጠቃ በጥሩ ሁኔታ ያለ

2.        

ሙቲካ የእንሰሳት መኖ ሳር ዝርያ

ግንጣይ

70 000

በበሽታና በተባይ ያልተጠቃ በጥሩ ሁኔታ ያለ

3.        

የሮደስ ሳር መኖ ዘር

ኪሎ ግራም

50

ጥራቱን የጠበቀና የዘር ብቅለት መጠኑ ከ90% በላይ የሆነ

4.        

የአልፋልፋ እንሰሳት መኖ ዘር

ኪሎ ግራም

70

ጥራቱን የጠበቀና የዘር ብቅለት መጠኑ ከ90% በላይ የሆነ

5.        

የእርግብ አተር ዘር

ኪሎ ግራም

125

ጥራቱን የጠበቀና የዘር ብቅለት መጠኑ ከ90% በላይ የሆነ

6.        

የትሪ ሉሰርን ዘር

ኪሎ ግራም

125

ጥራቱን የጠበቀና የዘር ብቅለት መጠኑ ከ90% በላይ የሆነ

ማስታወሻ፤ ድርጅቱ የሚገዛው የዘር የሳር ግንጣይ መጠን ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ መጠንና በድርጅቱ በጀት ላይ በመመስረት ከላይ ከተጠቀሰው መጠን መጠነኛ ለውጥ ሊያደርግ ይችላል

ከተጫራቾች የሚጠበቅ መስፈርት

 • የዘመኑን (2013 ዓም) ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድና ከሚመለከተው የመንግስት አካል የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው ፤የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ቁጥር ያላቸው ፣የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን ይጠብቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዳቸውን ከታች በተገለጸው አድራሻ እስከ ማክሰኞ ምሌ 13 2013 ዓም ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ በትክክል መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
 • አቅራቢዎች በተጠየቁ ጊዜ የሚያቀርቡትን የዘር ናሙና እና የማምረቻ ማሳቸውን ለማሳየት ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
 • ጨረታው የጨረታው መዝጊያ ቀን በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት በድርጅቱ ጨርታ ኮሚቴ አማካኝነት ተከፍቶ አሸናፊነት በአድራሻቸው የሚገለጽላቸው ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡

አድራሻ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከመገናኛ ወደ ሲምሲ መንገድ ሲቪል ሰርቪስ አለፍ ብሎ ከጊብሰን ት/ቤት ፊት ለፊት ጎልጎታ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ  ስልክ ቁጥር 011-647-72-33/34/35፣ ሞባይል፥ 0911704165 ወይም ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ወላይታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቦዲቲ ከኮንዶሚኒየም ጀርባ 0465591014፣ 0920172047።

Send me an email when this category has been updated