ሶሬቲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ህንፃ ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህንፃ ግንባታ ሥራዎችና የሆቴል ቤት እቃዎች አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡

soreti-logo

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 08/07/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/24/2021

Description

 ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሶሬቲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ሰሚት ሳፋሪ አካባቢ እያስገነባ ባለው B+G+5 ቅይጥ አገልግሎት ህንጻ ላይ እና በአዳማ ከተማ ደራርቱ አደባባይ አካባቢ እያስገነባዉ ባለው B+G+7 የሆቴል አገልግሎት ህንፃ ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህንፃ ግንባታ ሥራዎችና የሆቴል ቤት እቃዎች አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡

1ኛ. አዳማ የB+G+7 የሆቴል አገልግሎት ህንፃ ላይ

 • የሰዎች መመላለሻ ሊፍት አቅርቦትና ገጠማ (በቁጥር 2)
 • የሲሲቲቪ (ሴኩሪቲ ካሜራ) አቅርቦትና ገጠማ
 • የመፀዳጃ ቤት የዉሃና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ (Sanitary Work)
 • የውሃ ስርገት መከላከያ አቅርቦትና ገጠማ
 • የእሳት አደጋ መከላከያ አቅርቦትና ገጠማ
 • የሆቴል መፀዳጃ ቤት እቃዎች (ግዢ)
 • ልዩ ልዩ የሆቴል ቤት ኤሌክትሪክ ፊክስቸሮች (ግዢ)

2ኛ. አዲስ አበባ B+G+5 ቅይጥ አገልግሎት ህንጻ ላይ

 • የሰዎች መመላለሻ ሊፍት አቅርቦትና ገጠማ
 • የእሳት አደጋ መከላከያ አቅርቦትና ገጠማ
 • የፊኒሺንግ ሥራ (ፖርስሌን ወለል፣በርና መስኮት ሲል፣የደረጃ ግራናይት …)
 • የሲሲቲቪ (ሴኩሪቲ ካሜራ) አቅርቦትና ገጠማ
 • የሆቴል መፀዳጃ ቤት እቃዎች (ግዢ)
 • ልዩ ልዩ የሆቴል ቤት ኤሌክትሪክ ፊክስቸሮች (ግዢ)

በመሆኑም በዚህ መስክ የተሰማራቹህ ባለሙያዎች የዘመኑ ግብር የከፈላችሁበት ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሪጅናልና ኮፒ በመያዝ የማይመለስ 50.00 (ሃምሳ )ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 14 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ማለትም (ከነሃሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሃሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም) 6፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱንና ዲዛይኑን ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ድረስ በመምጣት መውሰድ የምትችሉ ሲሆን  በዛኑ ቀን ማለትም ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም)  ከሰዓት 8፡00 ሰነዱን በመመለስ በተመሳሳይ ቀን በ 8፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡

ማሳሳቢያ

 • ተጫራቾች ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ የድርጅታቸዉን ፕሮፋይል (የሥራ ልምድ) የሚያሳይ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ጨረታዉን ከመሙላታቸዉ በፊት ስራዎቹን ሳይቶቹ ድረስ በመሄድ መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሥራ ብቻ የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

Send me an email when this category has been updated