ሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ለህብረተሰብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል እስከ 4000ሜትር ርዝመት የሚደርስ የፕላስቲክ ትቦ/HDP 2″ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Plastics & Plastic Products
- Posted Date : 08/03/2022
- Phone Number : 0468830266
- Source : Reporter
- Closing Date : 08/16/2022
Description
የፕላስቲክ ትቦ/HDP 2″ አቅርቦት/ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለህብረተሰብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል እስከ 4000ሜትር ርዝመት የሚደርስ የፕላስቲክ ትቦ/HDP 2″ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉና በሽያጭ ማቅረብ የምትችሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ::
- አሸናፊው ሻጭ/አቅራቢ ዕቃውን በተፈለገው ጊዜ አስረክቦ ሲያጠናቅቅ የአሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ ሕጋዊ ደረሰኝ በማቅረብ ክፍያውን ይረከባል’ተገቢው የመንግስት ታክስም ተቀናሽ ይሆናል ::
- ተጫራች ለጨረታው የሚያቀርበውን የጠቅላላ ዋጋ 1% ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅበታል::
- ተጫራቹ ይህ ጨረታ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዕቃውን የምትሸጡበትን የአንዱን ሜትር ዋጋ በድርጅታችሁ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በ10/አስር/ ተከታታይ ክፍት የሥራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የድርጅታችን ቅጥር ግቢ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታዉ ሳጥን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚከፈተዉ በድርጅታችን ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ክፍት የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-ሶዶ ቡኢ የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት% ቡኢ ከተማ ‘ሶዶ ወረዳ’ ጉራጌ ዞን’ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103ኪ.ሜ በአለምገና-ቡታጅራ/ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ፡፡
የስልክ ቁጥር፡ 046-8830266 ወይም 0468830265 ወይም 0468830350 ወይም 0468830023