ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ በፒሊፕስ ልሙጥ አንደኛ ደረጃ ጨርቅ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊው ድርጅት እንዲሰፋለት ይፈልጋል

Sodo-Buee-Child-and-family-development-charity-logo-reportertenders-2

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0468830266
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/09/2022

Description

የተማሪዎች ዩኒፎርም ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ500 በላይ ለሚሆኑ   ታቃፊ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ በፒሊፕስ ልሙጥ አንደኛ ደረጃ ጨርቅ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊው ድርጅት እንዲሰፋለት ይፈልጋል በመሆኑም ፡-

 1. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ሆነው በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ለሰሩአቸው ስራዎች ከታወቀ ድርጅት ወይም መስሪያ ቤት የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ፡፡
 2. አሸናፊ የሆነ ተጫራች በቂ የስራ ቦታ ፤ የሰው ሀይል እና በቂ ማሽኖች  ኖሮት የተደራጀ መሆኑን በተጨባጭ ማሳየት የሚችል መሆን ይጠበቅበታል ፡፡
 3. ተወዳዳሪዎች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ህጋዊ ፍቃድ እና  የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን  የሚገልጽ ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በሲፒኦ በድርጅታችን ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
 5. ተጫራቾች የማይመለስ ሁለት ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ቡኢ ከተማ ከሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ህትመት ገጽ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ  በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 ሰዓት  እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት በመክፈቻው ቀን ደግሞ እስከ 6፡00  ሰዓት ድረስ ብቻ መግዛት ይችላሉ  ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሲያቀርቡ የጨርቅ ዋጋን ጨምሮ በአጠቃላይ ስራውን አጠናቆ የሚያስረክቡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከናሙና ስራ ጋር ማህተም በማሳረፍ  ቡኢ ከተማ በሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት  የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የስራ ቀን ላይ ከቀኑ 6፡30 ላይ ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት  ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡኢ ከተማ ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል ፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                             ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር

   046-883-0266/0350/0023 (ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት)

 ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡-

ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት፡ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ  ቡኢ ከተማ  ወደ አይመለል በሚወስደው መንገድ ከዋናው አስፓልት መንገድ 100 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ ቡኢ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምህራብ አቅጣጫ ከአለምገና ወደ ቡታጅራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ በ103 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡