ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት ደብተሮችን, ኬኒያ ቢክ እና ቡና እስክሪብቶዎችን, እርሳሶችን በየትምህርት ክፍል ደረጃቸው የሚያስፈልጋቸውን መጠን መግዛት ይፈልጋል

Sodo-Buee-Child-and-family-development-charity-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 07/27/2022
 • Phone Number : 0468830266
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/05/2022

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

 ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለ2015 ዓ.ም/ የትምህርት ዘመን የድርጅቱ  ታቃፊ ለሆኑ ተማሪዎች  ፕላስቲክ ሽፋን ሆነው የተለበዱ ሲናር ላየን ደብተሮችን፡- 1ኛ, ባለ 50 ቅጠል ባለ መስመር ፤ 2ኛ, ባለ 32 ቅጠል  ባለ መስመር 3ኛ, ስኩዌር ባለ 50 ቅጠል ደብተሮችን 4 ኛ,ኬኒያ ቢክ እና ቡና እስክሪብቶዎችን፣ 5ኛ, HB እርሳሶችን  በየትምህርት ክፍል ደረጃቸው የሚያስፈልጋቸውን መጠን መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ፡-

 1. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ሆነው በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ  ይኖርባቸዋል ፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 / አምስት ሺህ ብር/ በሲፒኦ በድርጅታችን ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከድርጅቱ በ 200 ብር በመግዛት ከላይ በቅደም ተከተል የተጠቀሱትን 5 አይነት የግዢ ዝርዝሮችን በድርጅታቸው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የእያንዳንዱን እቃ  ነጠላ ዋጋ  እስከነ ቫቱ  በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ኤነቨሎፕ  የተጠየቁትን ሰነዶች በማሸግ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር  ህትመት ገጽ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ  ቀናቶች ውስጥ  በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ  ተገኝተው   ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ፡፡
 4. ተጫራቾች በተጨማሪም የጨረታውን ሰነድ ሲያቀርቡ ከሚያቀርቡት ከላይ ከተገለጹት ደብተሮች፤ እስኪርብቶዎች እና እርሳሶች ለናሙና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ በኤንቨሎፕ አሽገው ቡኢ ከተማ በሚገኘው የሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት  የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
 5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የስራ ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት  ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡኢ ከተማ ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል ፡፡
 6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

   ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር

   046-883-0266/0350/0023 (ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት) ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡-

ሶዶ ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት፡ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ  ቡኢ ከተማ  ወደ አይመለል በሚወስደው መንገድ ከዋናው አስፓልት መንገድ 100 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ ቡኢ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምህራብ አቅጣጫ ከአለምገና ወደ ቡታጅራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ በ103 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡