በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

belayab-motors-logo

Overview

 • Category : Spare Parts Sale & Supply
 • Posted Date : 01/14/2023
 • Phone Number : 0966215183
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/27/2023

Description

የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም:-

የሲኖ ትራክ(SINO Truck)፤የኒሳን ዩዲ(Nissan UD)፤ የፉቶን ዳምፕ ትራክ(Foton Dump Truck) ፤ ፎርክሊፈት(Forclift)፤ የሎደር (Loader) ፤የኤክስካቫተር(Excavator) ፤የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control)  የዳምፐር(Damper)፤የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ(ZNA pick up)፤ሪች(Rich) ፤የ ቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick up)፤የፎቶን ፒክ አፕ(Foton pick up)፤የፎርላንድ (Forland)፤የፋዎ ቤላ(FAW BELLA)፤የኦቲንግ(Oting)፤የፎቶን ሚኒ ባስ(Foton mini Bus)፤ ሙዳን ባስ(Mudan Bus) ፤ኤፍሲአር(FSR)፤ጋርቤጅቲፐር(Garbage Tipper)፤ካኒባላይዝ(Canibalize) እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

 • የጫረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጫረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ ብሄራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል፡፡
 • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ) በባንክ በተረጋገጠCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
 • አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡
 • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ ከሚገኘው የበላይአብ ሞተርስ ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሞባይል ፡-0966 21 51 83/84

ስልክ ፡- 0114 71 54 48

ፋክስ ፡- 0114 71 53 31

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ