በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ ማህበር የተለያዩ የጫማ ማምረቻ ማሽነሪዎችን የዋጋ ትመና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ እና በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድና ልምድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሽነሪዎቹን ወቅታዊ በሆነ ዋጋ ማስገመት ይፈልጋል።

belayab-motors-logo

Overview

 • Category : Machinery Purchase
 • Posted Date : 11/10/2021
 • Phone Number : 01143943691
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/01/2021

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ ማህበር የተለያዩ የጫማ ማምረቻ ማሽነሪዎችን  የዋጋ ትመና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ እና በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድና ልምድ ያላቸውን ተጫራቾች  አወዳድሮ ማሽነሪዎቹን ወቅታዊ በሆነ ዋጋ ማስገመት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ የንግድፈቃድ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የተሰጠ ክሊራንስ፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር፣እና የተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገቢያ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ጉዳዩ ከሚመለከተው ባለስልጣን መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) 10,000 (አሥር ሺህ) ብር በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO)፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታው ዶክመንቱን የማይመለስ 100 (አንድመቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ላይ ስራውን አጠናቀው የሚየስረክቡበትን የጊዜ ገደብ  በግልፅ መጥቀስ ይኖርባችዋል፡፡
 6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 7. ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ በስልክ ቁጥር፡- 0114 394 36 91 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ካዲስኮ የቀድሞ የጀማይካ ጫማ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ

በላይአብሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማ