በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18-02B) የ PPR pipe, Fittings and UPVC Materials ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-1

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 10/05/2022
 • Phone Number : 0118721174
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/15/2022

Description

የጨረታ ቁጥር ፕሮ/18-02B/4476/15

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18-02B) ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የሥራ ዝርዝር (Specification) መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የ PPR pipe, Fittings and UPVC Materials ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ. የሥራ ዝርዝር የጨረታ ቁጥር የጨረታ መዝጊያ ቀን የጨረታ መክፈቻ ቀን
1 PPR pipe, Fittings and UPVC Materials ፕሮ/18-02B/4476/15 05/02/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 05/02/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡15

ስለሆነም፡-

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረበ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቆሬ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት ከአቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 05/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ጥቅምት 05/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
 7. አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 8. ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

መከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት 18-02B

ቆሬ አደባባይ

ለበለጠ መረጃ፡- 011-8-72-11-74 ወይም 0911-69-13-78