በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ምዕራፍ II ግንባታ ፕሮጀክት (Compound Light Pole and Fittings) ከታች በተገለፀው የስራ ዝርዝር መሰረት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-4

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/09/2022
 • Phone Number : 0911648680
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/21/2022

Description

  የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ምዕራፍ II ግንባታ ፕሮጀክት /16-01B/ በሰሚት አካባቢ እየገነባቸው ለሚገኘው የአፓርትመንት ህንፃዎች አገልግሎት የሚውል የጊቢ ውስጥ መንገድ መብራት (Compound Light Pole and Fittings) ከታች በተገለፀው የስራ ዝርዝር መሰረት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1 Compound Light Pole & Fitting Unit  Qty
1.1 Supply  hot-dip galvanized cylindrical offset mast with 3 m over ground height and 0.6m planting depth type siteco 5NY 231 6-30AM00 or approved equivalent. No    88.00
1.2 Compound Light Fitting Type Siteco 5NA 582 2-3 with  1xHSE 70W/E high pressure sodium vapor Lamp or approved equivalent No    88.00

ስለሆነም ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ በመክፈል ከፕሮጀክት ፋይናንስ ከላይ በዝርዝር በተገለጸው መሰረት የመጫራቻ ሰነዳችሁን አዘጋጅታችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት /አየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ጀምሮ ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ ጨምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አሥር) የሥራ ቀናት በፕሮጀክት ግዥ እና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታው ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 04:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 04:30 ሰዓት ላይ ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የቴክኒካል ሰነድ ላይ አስፈላጊው ግምገማ ከተከናወነ በኋላ የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈትበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች፡-

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (tax clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፤
 2. በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበርያ የዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፤
 3. የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ የተወካይ ሙሉ ስም እና ፊርማ እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በመመሪያው ለይ በተገለፀው መልኩ በታሸገ ኢንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 4. በዘረፉ በቂ ለምድ ያላቸው መሆን አለባቸው
 5. የየቴክኒካል እና የፋይናንሻል መጫረቻ ሰነዶች ለየብቻው ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፣
 6. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የመልካም ስራ ዋስትና Unconditional Bank Guarantee ወይም CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 7. ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ሰሚት ኮንዶሚኒየም 2 በር ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሎ

ስ/ቁ: 0911648680 ወይም 0924-32-52-62

ከሠላምታ ጋር

ፕሮጀክቱ