በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የሚገኘው ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር በስሩ ለሚገኙ 4 ማዕከላትና አንድ ማስተባበሪ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ፣የቢሮ ዕቃዎች ፣እስቴሽነሪ ፣የፅዳት ዕቃዎችና የህትመት ሰነዶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 01/04/2023
 • Phone Number : 0116629510
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/16/2023

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የሚገኘው ፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር በስሩ ለሚገኙ 4 ማዕከላትና አንድ ማስተባበሪ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ፣የቢሮ ዕቃዎች ፣እስቴሽነሪ ፣የፅዳት ዕቃዎችና የህትመት ሰነዶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

 1. ተጫራቾች በዘረፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ ፣የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ከፍያ ማረጋገጫ የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆኑ ከማዕከላችን ከ17/18 ህ/ል/ማዕከል የሚገዙ እቃዎችን ስም ዝርዝርና ብዛት የያዙ ሰነዶች በመግዛት ቫትን ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች አሻሚና ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር (ለመወዳደር መሞከር) ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
 3. ሰነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንድ በላይ ማስገባት አይችሉም፡፡
 5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ፖስታ በሰም ታሽጎ ፓስታዎቹ ላይ አድራሻና የድርጅቱን ስም በመጻፍ ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ እና በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው በወጣበት በአስረኛው ቀን ከጧቱ ከ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሣጥን ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የ17/18 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል፡፡ መያያዝ ያለበት በዘረፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ከፍያ ማረጋገጫ የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 7. የጨረታው ሳጥን ከታሸገና ሰነዶቹ መከፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
 8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ባሸነፈው የዕቃ ልክ መሰረት በአድራሻው በስሙ ቼክ ተሰርቶለት ዕቃውን ገቢ ሲያደርግ ክፍያ ይፈፀምለታል ሆኖም ለክፍያው ህጋዊ ደረሰኝ የድርጅቱን ቲን ቁጥር አስገብቶ ይቆርጣል፡፡
 9. ዕቃዎቹን ከሚጠበቀው ከፍተኛ ጥራት እና ብዛት በተፈለገው መጠን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ወረድ ብሎ በድሪያ ሞል ፊት ለፊት 17/18 ህ/ል/ማዕከል ግቢ ውስጥ

ለበለጠ መረጃ          0116 629510/0116 186352/0116 622196