በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር መድሀኒቶችን፤ የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ላብ ሪኤጀንቶችንን እና የተለያዩ የህክምና ግብአቶችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

Family-Guidance-Association-of-Ethiopia-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Medical/Laboratory Equipment
 • Posted Date : 07/03/2021
 • Phone Number : 0114672300
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/19/2021

Description

በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

መድሀኒቶችን፤ የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ላብ ሪኤጀንቶችንን እና የተለያዩ የህክምና ግብአቶችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ለትርፍ ያልተቋቋመ እና የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በ1958 ዓ.ም. የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ማኀበሩ በውመን ኢንተግሬትድ ሴክሹዋል ሄልዝ ፕሮጀክት (WISH – Project) ባገኘው የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በየአካባቢ ፅ/ቤቶቹ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ማህበሩ በዊሽ ፕሮጀክቱ ስር ለሚያከውናቸው የየተዋልዶ ጤና ህክምና ተግባራትን ለማስፋፋት እንዲረዱት እና የኮቪድ-19 የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል እንዲያግዘው  የተለያዩ መድሀኒቶችን (DRUGS)፤ የኮቪድ መከላከያ ግብአቶችንን (PPE MATERIALS)  የላብራሪ ማሽን ሪኤጀንቶችን (LAB REAGENTS) እና የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን (CLEANING MATERIALS) ህጋዊ እና በየዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸውን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መሰረት መድሀኒቶችን (DRUGS)፤ የኮቪድ መከላከያ ግብአቶችን (PPE Materials)  የላብራቶሪ ማሽን ሪኤጀንቶችን (LAB-REAGENTS) እና የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን (CLEANING MATERIALS) ማቅረብ የምትፈልጉና መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ሠነድ በማይመለስ ብር 10ዐ.ዐዐ በመግዛት በጨረታው እንደትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

ተጫራቾች

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
 2. ቫት የተመዘገቡና የቫት ሰርተፍኬትና የታክስ ክሊራንስ ሰርፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
 3. ተጫራቾች ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሠነድ የማኀበሩ ዋና መሰሪያ ቤት በመቅረብ በመግዛት የሚችሉ
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በተገቢው መሰረት ሞልተው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ እንደዚሁም አጠቃላይ ያቀረቡትን ዋጋ ድምር 1% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለብቻው ካሸጉ ቡሃላ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ከተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቁያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከሰኔ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ማስገባት ይችላሉ፤
 5. ጨረታው ሰኞ ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱና በሰአቱ ለመገኘት በፈቀዱና በተገኙ ተጫራቶች ወይም በሰአቱ በተገኙ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት በእለቱ ከሰአት ቡሃላ በ8፡0ዐ ስዓት ይከፈታል፡፡
 6. ማኀበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡
 7. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

አድራሻ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ፖ.ሳ.ቁጥር 5716

ስልክ ቁጥር ዐ1146723ዐዐ

ሪቼ መስከረም ማዞሪያ 2ዐዐ ሜትር ገባ ብሎ

Send me an email when this category has been updated