በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለጸውን ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈለጋል።

Ethiopian-Tewahido-Church-logo-Reportertenders-5

Overview

  • Category : House & Building Furnishings & Fixtures
  • Posted Date : 04/24/2021
  • Phone Number : 0111270054
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/07/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለጸውን ሥራ ለ2013 ዓ.ም የስራ ዘመን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፣ የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አባል ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈለጋል።

ሎት

የሥራው ዓይነት

ሥራው የሚከናወንባቸው የሕንጻዎች ስም

ተፈላጊ ሥራ ዘርፍ

ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ዋስትና

1

የአልሙኒየም ሥራ

G+4 የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ሕንጻ

በአልሙኒየም አቅርቦትና ግንባታ ሥራ ህጋዊ ፍቃድና መልካም የሥራ አፈጻጸም ያላቸው

20,000.00

2

የመረጃ መረብ መሠረተ ልማት አቅርቦትና ዝርጋታ ሥራ (supply& installation Data network infrastructure)

ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ለሚገኙ አራት ሕንጻዎች

የመረጃ መረብ መሠረተ ልማት አቅርቦትና ዝርጋታ ሥራ  ህጋዊ ፍቃድና መልካም የሥራ አፈጻጸም ያላቸው

20,000.00

ስለዚህ ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ ይህ ጨረታ በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የኢ/ኦ/ተ/ቤ ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 72 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛትና መወዳደር የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ግንቦት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ግንቦት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን

ሀ) ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሰነዶችን ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል

ለ) ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት የውድድሩን አፈጻጸም መከታተል ይገባቸዋል።

ማሳሰቢያ፥- ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቱ የተሻል አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት

ስልክ ቁጥር 011-1270054/011-1565950 አራት ኪሎ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ግቢ