በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ

EOTC-CFAO-logo

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 01/16/2021
 • Phone Number : 0911620861
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/26/2021

Description

የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት እ.ኤ.አ የ2020  የዋና መ/ቤት እና በሥሩ የሚተዳደሩ 18 የሕፃናት መርጃ ማዕከላትና የኅብረተሰብ ልማት ፕሮጀክቶች፣ የምግባረ ሠናይ ጠቅላላሆስፒታል ሒሳብ በተናጠል በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ከእያንዳንዱ ኦዲት ሪፖርት በተጨማሪ በተናጠል ኦዲት ተደርገው የተዘጋጁትን የሒሳብ መግለጫዎች ተዛማጅ መረጃዎችና ICM አስፈላጊዎቹ ማስተካከያዎች ተደርገው በድርጅቱ ደረጃ የተጠቃለለ (Consolidated) ኦዲት ሪፖርት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ የኦዲቲንግ ባለሙያ ድርጅቶች፡-

 1. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላችሁ፤
 2. የዘመኑን ግብር ከፍላችሁ የኦዲት ሥራ ፈቃድ ያሳደሳችሁ፤
 3. የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ፤
 4. ለሥራው የሚመጥኑ  በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ያሏችሁ፤

አስፈላጊ ማስረጃዎቻችሁን አያይዛችሁ

 1. ስንት ዓመት የሥራ ልምድ እንዳላችሁ/ የድርጅታችሁን ፕሮፋይል፤
 2. ለሥራው በአንድ ጊዜ ልታሰማሯቸው የምትችሉን የቡድን ብዛት፣ የእያንዳንዱ የቡድን አባላት ብዛትናሙያ ብቃት መግለጫ፤
 3. በተናጠል ለሚመረመረው ለእያንዳንዱ ሪፖርት እና የተመረመሩትን ሪፖርትበድርጅቱ ደረጃ ለማጠቃለል (Consolidate) ለማድረግ የምታስከፍሉት ጠቅላላ ገንዘብ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የትራንስፖርትና የውሎ አበል ተለይተው ይቅረብ፤
 4. የአከፋፈል ሁኔታ (Terms of payment)
 5. ሥራውን አጠናቅቃችሁ ሪፖርቶቹን (ICM) ጭምር የምታቀርቡበትን ጊዜ፤

በመግለፅ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ በአሥር ተከታታይ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጽ/ቤታችን ሒሳብ ክፍል ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

የመጫረቻ ሰነዱን ለማዘጋጀት ስለሥራው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከድርጅታችን ፋይናንስ አገልግሎት በቅድሚያ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ድርጅቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

በቀን በሰው ተብለው የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች ለንፅፅር ስለማያመቹ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

አድራሻ፡አራት ኪሎ ከሚገኘው ማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ

ግንፍሌ ድልድይ አጠገብ፤

ስልክ፡- 09 11 62-08-61/ 011-123-87-52

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት

 

Send me an email when this category has been updated