በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ-ኢየሱስ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ መነሃሪያ አካባቢ ያስገነባው ዘመናዊ የእንግዳ ማረፊያ አፓርትመንት (G+7) በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና አቅም ላላቸው ባለሃብቶች ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Rent
- Posted Date : 01/11/2023
- Phone Number : 0118337484
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/08/2023
Description
የእንግዳ ማረፊያ አፓርትመንት ለማከራየት የወጣ የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
- በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ-ኢየሱስ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ መነሃሪያ አካባቢ ያስገነባው ዘመናዊ የእንግዳ ማረፊያ አፓርትመንት (G+7) በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና አቅም ላላቸው ባለሃብቶች ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
- በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ-ኢየሱስ ሐዋሳ ከተማ መነሃሪያ አካባቢ ያስገነባው ዘመናዊ የእንግዳ ማረፊያ አፓርትመንት በኪራይ የጨረታ ቁጥር 001/2015 ሙሉ በሙሉ ያከራያል፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ አፈጻጸም የተዘጋጁትን የጨረታ ሠነዶች አዲስ አበባ በሚገኘው የኢ/ወ/ቤ/መካነ-ኢየሱስ የጡረታ ኢንሹራንስና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጽ/ቤት ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 በመቅረብ የጨረታ ሠነድ ተመላሽ የማይደረግ ብር 300.00 (ብር ሦስት መቶ) በመክፈል ከጥር 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-11፡00 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፕሮፖዛላቸውን ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ፣ የተጫረቱበትን ድርጅት ስምና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ የካቲት 1/2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 በቢሮ ቁጥር 410 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮሚሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው የሚቀርበው በሚከተለው አድራሻ ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ-ኢየሱስ የጡረታ፣ ኢንሹራንስና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 መካኒሳ ታክሲ ተራ ፊትለፊት መካነ-ኢየሱስ ህንጻ 4ኛ ወለል
ስልክ፡- 0118-337484/ 09 04 64 54 40
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የጨረታ ቁጥር 001/ 2015 ድርጅት በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡