በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ባለ 28 ጌጅ ስፋቱ 1 /አንድ/ ሜትር የሆነ መጠኑ 250 ሜትር የአሸንዳ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 01/04/2023
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/20/2023
Description
የአሸንዳ ቆርቆሮ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ባለ 28 ጌጅ ስፋቱ 1 /አንድ/ ሜትር የሆነ መጠኑ 250 ሜትር የአሸንዳ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፣
- በዘርፉ የታደሠ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ዋናውንና ኮፒ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡትን ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- የጨረታ ዘነዱን በዘርፉ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ለአንዱ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ዘነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት በመቶ/ በባንክ በተመሰከረ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በታሸገ ኤንቨሎኝ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ቢሮ ቁጥር G2 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፣
- አሸናፊዎች የጨረታ አሸናፊነቱ /አሸናፊነታቸው/ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ካልፈረሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለዘርፉ ገቢ ይደረጋል፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔሲፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ዘርፉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06
ስልክ ቁ. 0911166473/0912185337/0912150832
ደብረዘይት መንገድ ከፋፋ የምግብ አክሲዮን ማኀበር በስተጀርባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የእርሻ መምሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ