በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኀበር ያገለገሉ ብዛታቸው 4 የሆነ ሲኖ ትራክ ሞዴል ZZ42 ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ከነተሳቢያቸው እንዲሁም 1 አውቶ ብስ መኪና ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

bechalcha-transport-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 09/17/2021
 • Phone Number : 0221111791
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/01/2021

Description

ያገለገሉ ሲኖ ትራክ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች እና ማርቼዲስ አውቶ ብስ መኪና ሽያጭ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 04/2021

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኀበር ያገለገሉ ብዛታቸው 4 የሆነ ሲኖ ትራክ ሞዴል ZZ42 ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ከነተሳቢያቸው እንዲሁም 1 አውቶ ብስ መኪና ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እ.ኤ.አ እስከ 30/09/2021 ወይም መስከረም 20/2014 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ ካዲስኮ ሕንጻ ፊት ለፊት በሚገኘው ማ/ጽ/ቤት ወይም ናዝሬት ሶደሬ መንገድ በሚገኘው የአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት በመቅረብ የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር፣ የጨረታ መነሻ ዋጋ፣ ዝርዝር የሽያጭ መረጃና መስፈርት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍሎ በመግዛት ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ናዝሬት በሚገኘው ዋናው መ/ቤታችን በግንባር ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% በባንክ በተመሰከረለት CPO በጨረታው መክፈቻ ሰአት ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ማስያዝ የሚኖርባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውም ለተሸናፊ ተጫራቾች ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን የአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉበት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን በሙሉ ወይም በከፊል ለመግዛት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 4. ጨረታውም እ.ኤ.አ በ01/10/2021 ወይም በ21/01/2014 ዓ.ም ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ በሰራተኞች ክበብ አዳራሽ ውስጥ በግልጽ ተከፍቶ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ተሸጠው እስኪጠናቀቁ ድረስ በየሳምንቱ አርብ አርብ ቀን ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰአት ጨረታው ይቀጥላል፡፡
 5. በጨረታው ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ ለአ/ማህበሩ ገቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ይህንን ያላደረገ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለአ/ማህበሩ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
 6. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ተሽከርካሪ ሙሉ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ ያለበት ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተሽከርካሪውን ለማንሳት ያልቻለ የጨረታ አሸናፊ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በቀን ብር 100፡00 /አንድ መቶ ብር/ የማቆያ ኪራይ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
 7. ተሽከርካሪዎቹ የሚፈለግባቸው ማንኛውም ቀረጥና ውዝፍ እዳ ቢኖር በአ/ማህበሩ ይሸፈናል፡፡ ነገር ግን የስም ማዛወሪያን እና የቦሎ ክፍያ በገዢው በኩል ይከፈላል፡፡
 8. ተጨማሪ ዝርዝር የሽያጭ ሁኔታና የጨረታ መመሪያ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ በግልጽ ይቀመጣል፡፡
 9. /ማኀበሩ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 022-111 17 91 ናዝሬት 0114-42 27 11 ወይም 0114-43 13 48 ይደውሉ፡፡

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር