በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን የግብርና ግብዓት ኬሚካል ምርቶችን በየክልሎች ለማከፋፈል ፍላጎት ካላቸው ግለሰቦች፣ማህበራት ወይም ነጋዴዎች ጋር በማወደደር መርጦ በውል ስምምነት አብሮ ለመስረት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Pesticides & Insecticides
 • Posted Date : 09/11/2022
 • Phone Number : 0116333298
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/03/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር APPF/03/14

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን የግብርና ግብዓት ኬሚካል ምርቶችን በየክልሎች ለማከፋፈል ፍላጎት ካላቸው ግለሰቦች፣ማህበራት ወይም ነጋዴዎች ጋር በማወደደር መርጦ በውል ስምምነት አብሮ ለመስረት ይፈልጋል፡፡

 የምርቶች ዝርዝር

      ሀ. የፀረ ነፍሳት (insecticide) 

      ለ. የፀረ-አረም (herbicide)

      ሐ. የፀረ-በሽታ (fungicides)

      መ. የእንሰሳት የውጭ አካል ጥገኛ ህክምና(animals ecto parasite ) ናቸው፡፡

ስለዚህ ፍላጎት ያለቸው ተወዳደሪዎች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 1. ፋብሪካው የሚያመርታቸው የግብርና ግብአት ኬሚካሎች በሙሉ ወይም በከፊል በጅምላ አከፋፋይነት በቂ ልምድ ኖሮት ከሚያከፈፍልበት አካባቢ የተሰጠውን የፀረ-ተባይ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን የኖርበታል፡፡
 2. የኬሚካል ምርቶቹን ለተጠቃሚው ማህበረሰብና ለክልል ከተሞች ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ በጨረታ መመሪያ ውስጥ በዝርዝር የሰፈሩትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
 3. ምርቶቹን/ቱን ከፋብሪካው ለመግዛት የሚያስችል በቂ የስራ ማስኬጃ/መዋዕለ ነዋይ ሊኖረው ይገባል፡፡
 4. ተጫራቾች ወይም ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ አዳሚ ቱሉ ዋና መ/ቤት ንግድ ቢሮ ወይም ቦሌ ጅቡቲ ኢምባሲ አካባቢ ከዋናው መንገድ ሀምሳ ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኝ የማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 1,000,000.00( አንድ ሚሊዮን ብር) በሲፒኦ (CPO ) አስይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች የጨረታ መመሪያው ላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ማስረጃዎች ከጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ  (CPO ) ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ በተጠቀሱት የፋብሪካው የስራ ቦታዎች ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሳለሳ የስራ ቀናት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
 7. ጨረታው 31 (በሳለሳ አንደኛው) ቀን ከቀኑ 7፡30 ላይ ቦሌ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊለፊት በሚገኘው አዲስ አበባ ማስተባበሪ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ፋብሪካው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ፡፡

አድራሻ፡  0116333298  ፡ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

       0464419164 ፡ አዳሚ ቱሉ ዋና መስሪያ ቤት

 ፖ.ሣ.ቁ 247    ፡ አዳሚ ቱሉ

0468410447 ፡ ንግድ መምሪያ ቢሮ

            0911687800  ፡ የንግድ መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ