በውስጣዊ ግጭቶትና ሌላ የተፈጥሮና ዓለም አቀፍ ቀውስ ተፅኖ ስር ያሉ ፥ እድገት ተኮር የሆኑ የኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ ድርጅቶችን ቀጣይነት ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም የፍላጎት መግለጫ ጥሪ

Giz-office-Logo-2

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/31/2022
 • Phone Number : 0943666586
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/31/2023

Description

በውስጣዊ ግጭቶትና ሌላ የተፈጥሮና ዓለም አቀፍ ቀውስ ተፅኖ ስር ያሉ ፥ እድገት ተኮር የሆኑ የኢትዮጵያ

አነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ ድርጅቶችን ቀጣይነት ለማገዝ የታቀደ ፕሮግራም

የፍላጎት መግለጫ ጥሪ

የጀርመን ቴክኒካል ትብብር (ጂ.አይ.ዜድ) በአሁን ወቅት “የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ ኢኮኖሚ ማሳደግ”( PSD-E) የተሰኘን ፕሮጀክት የማስፈፀም ተልዕኮ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር (BMZ) በመውሰድ እየሰራ ይገኛል ። በዚህም ፕሮጀክቱ በሚያመቻቸው የተሻለ የእድገት አጋጣሚ ፤ አነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ ድርጅቶች እንዲሁም እድገት ተኮር የሆኑ ጀማሪና አነስተኛ ድርጅቶች ይታገዙ ዘንድ ታልሟል። የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ ኢኮኖሚ ማሳደግ (PSD-E) ፕሮጀክት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን፣ ጀማሪዎችን እና አነስተኛ ዕድገት ተኮር ኩባንያዎችን ከተሻሻሉ የዕድገት እድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን ይህም አምስት ንዑስ ፕሮጀክቶችን (Outputs) በመጠቀም ተግባራዊ ይሆናል።

ሴኳ(sequa gGmBH) በግጭት እና በሌሎች ቀውሶች ለተጎዱ ለጥቃቅንና አነስተኛ እና ለስራ ፈጣሪዎች ቀጥተኛ ድጋፍ (SME Grant Facility) በመስጠት ላይ የሚያተኩረውን የPSD-E ፕሮጀክት (Output 5) ተግባራዊ ያደርጋል። በመርሃግብሩ በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 25 ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ አቅዷል። ሴኳ የአጋዥ ፕሮግራሙን ዕቅድ መሰረት በማድረግ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማገዝ የሚያስችል መርኃግብር ተግባራዊ ለማድረግ ተዘጋጅቷል። የአመልካች ድርጅት ማመልከቻዎች ፤ በዘርፉ ባለሙያዎች በሚደረግ የብቃት ማጣሪያ ሂደት ዉስጥ ማለፍ ይኖርባቸዋል። በቀጣይ የማጣራት ሂደቱን ያለፉ ድርጅቶች ከቢዝነስ እቅዳቸው አንፃር በባለሙያዎቹ ተመርምረው ድርጅታቸው ከጐደለው አንፃር ሊረዳ የሚችልበት ዕቅድ ይወጣል።

በዚህ ፕሮጀክት በሴቶች ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ለሴቶች የስራ እድል ስልጠና ልዩ ትኩረት ይሰጣል። የድጋፍ ፕሮግራሙ በዕቅዱ ለመሳተፍ ፍላጐት ላሳዮ አነስተኛና መካከለኛ የግል ድርጅቶች የተከፈተ ሲሆን ፤ እነዚህ ድርጅቶች ቢያንስ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሥራ ላይ የቆዮ ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ በቀዳሚው የበጀት ዓመት ብር 1,000,000 ወይም ከዝያ በላይ የሆነ ሽያጭ ያስመዘገቡ መሆን አለባቸው። መስፈርቶችን የሚያሟሉ አነስተኛና መካከለኛ የግል ድርጅቶች በቀጣይ ሁለት ዓመታት  በየዓመቱ ቢያንስ 10 ሰራተኞችን መቅጠር መቻላቸውን የሚያረጋግጥ የቢዝነስ ፕሮፖዛል ወይም ዕቅድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።

ለእገዛው የሚታጬ አመልካች ድርጅቶች በአካባቢያቸው በተከሰተ ውስጣዊ ግጭቶት፣ በኮቪድ 19 ፣ በዮክሬን ጦርነት ፣ በአየር ንብረትና የተፈጥሮ አካባቢ ቀውስ ተፅኖ ስር ያሉና ወረድብሎ በተመለከቱት እና ቀዳሚውን የድጋፍ ዕቅድ ያሳካሉ ተብሎ በታሰቡ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ይሆናሉ።

 1. በመሰረታዊ የምግብ አቅርቦት የተሰማሩ ድርጅችች፦ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ለማሻሻል ይቻል ዘንድ በመሰረታዊ የምግብ አቅርቦት ለምሣሌ በዳቦ ፣ በእንጀራ ፣ በውኃ ፣ በወተትና ተዋፅዎዉ ፣ በአትክልት ፣ በፍራፍሬና በመሰል የምግብ አቅርቦት የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን የሚያካትት ነው ።
 2. በውኃ፣ በጽዳት ጥበቃ፣ በንጽህና በመሰል መሰረታዊ አቅርቦት የተሰማሩ ድርጅችች፦ ይህ ታሳቢ በሆኑትና ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ያለውን ህዝብ በጤና አጠባበቅ ፣ በውኃ አቅርቦት ፣ በአካባቢና በግል ንጽህና አኳያ ያለን አቅርቦት ለማረጋገጥና ለማሻሻል በሚያስችል፣ እንዲሁም በግንባታ ግብዓት አቅርቦት፣ በማህበራዊ አገልግሎትና በመሰል የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን የሚያካትት ነው ።
 3. በዕቃ ጭነት፣ በህዝብ ማጓጓዣና በግንኙነት (ኮሙኒኬሽን)ቴክኖሎጂ (ICT) የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅችች፦ ይህም መሰረታዊ የዕቃና የአገልግሎት አቅርቦትን ፤ ጉዳት በደረሰባቸው ቀጠናዎች ማሻሻልና ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ፤ በተጠቃሾቹ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን የሚያካትት ነው።

በተጨማሪም፣ የሚከተሉትን የአመልካች መስፈርቶች በኦፊሴላዊ ህግ ወይም በተቋም ሰነዶች መረጋገጥ እና ማሙዋላት ይኖርባቸዋል ።

 1. ድርጅቱ ህጋዊ መሆን አለበት፣
 2. በኢትዮጵያ የተመዘገበ፣
 3. በተሰማራበት ስራ ቢያንስ ለሁለት አመት የቆየ፣
 4. አመልካች የግልድርጅት የሆነና በኢትዮጵያ የንግድ ምዝገባ ሕግ መሰረት የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል(መንግሥታዊ ያልሆነ)፣
 5. ድርጅቱ ቢያንስ 10 ቢበዛ እስከ 100 ሰራተኞችን ማስተዳደር ይኖርበታል፣
 6. ድርጅቱ የሚወዳደርበት ፕሮጀክት እራሱ መተግበር አለበት።

ለተመረጡ  ድርጅቶች የሚሰጠው እገዛ ሦስት መሰረታዊ አካሄዶችን የተንተራሰ ነው።  እነኝህም 1)የቢዝነስ ስልጠና እና የትግበራ ክትትል 2)የማምረቻ መሣሪያ – ማሽነሪ ግዥ 3)የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የልምድ ልውውጥ ትምህርታዊ መድረክ ናቸው።

የተጠቀሱትን የፕሮጀክቱ መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የሚያሟሉ የአነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ ድርጅቶች (SMEs) በኢሜል አድራሻ፡                               [email protected] ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ በአክብሮት እንጋብዛለን። የማመልከቻ ቅጾቹ በአመልካቾች ጥያቄ መሰረት ቀደም ሲል በተጠቀሰው ኢሜል አድራሻ ወይም አባል ከሆኑበት የክልሉ የዘርፍ ማህበራት ጽቤት ማግኘት ይችላሉ።

በተጨማሪም አመልካች ድርጅቶች የማመልከቻ ቅጹን ሞልተው እስከ ጥር 312023 ድረስ በተመሳሳይ ኢሜል አድራሻ ([email protected]) መላክ አለባቸው።

ከማመልከቻው ሂደት ጋር ለተያያዙ ማናቸውም ጥያቄዎች እና ድጋፎች እባክዎን +251 943 666 586 ይደውሉ።