ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. ያገለገለ መኪና ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 05/29/2021
- Closing Date : 06/14/2021
- Phone Number : 0114162621
- Source : Reporter
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. የድርጅቱ ንብረት የሆነውን ስቴሽን ዋገን፣ማሕንድራ የሠለዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A23915 አ.አ. ሞዴል ስኮርፒዮ የሆነዉን ያገለገለ መኪና ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 550,000.00 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲሆን፤
- የመኪውን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መኪናው ባለበት የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ከሚኘው ቶታል ማደያ ጀርባ ቤተ ሳይዳ ሕንፃ ቅጥር ግቢ በምድር ቤት የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ 3፡00-4፡00 ከሰዓት ከ 10፡00-11፡00 ሰዓት በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረበውን መኪና ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ስዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፐርሶኔል ክፍል 4ኛ ፎቅ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የመነሻ ዋጋ 10% ( አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በዋናው መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ሙሉ ክፍያ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ በመክፈል መኪናውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዘዋወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ክፍያዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-16-26-21 በመደወል ወይንም ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡