ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 10ኛ አስቸኳይ/ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Buussaa-Gonofaa-Microfinance-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/30/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/24/2022

Description

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ.

የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ስብሰባ ጥሪ

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 10ኛ አስቸኳይ/ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ. ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሄድ፣ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት በስብሰባዉ ላይ እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡

የ15ኛ መደበኛ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. የጉባዔዉን ጽ/ቤት መሰየም እና ምልዓተ-ጉባዔ መሙላቱን ማረጋገጥ፣
 2. የጉባዔዉን አጀንዳዎች ማፅደቅ፣
 3. የዲሬክተሮች ቦርድ የ2021/22 የስራ ክንዉን ሪፖርት መስማት እና ተወያይቶ ዉሳኔ መስጠት፣
 4. የ2021/22 የዉጭ ኦዲተሮችን የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት መስማት እና ተወያይቶ ዉሳኔ መስጠት፣
 5. ጁን 30 ቀን 2022 ስለተጠናቀቀዉ የ12 ወራት የሂሳብ ዓመት ትርፍ አደላደል ላይ መወያየት እና መርምሮ የዉሳኔ ሀሳብ መስጠት፣
 6. የጎደሉትን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሚተኩ የተተኪ አባላት ሹመጽ መወሰንና ማጽደቅ፣
 7. ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈለዉ ዓመታዊ የአገልግሎት አበል ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 8. ለመጪዉ ዘመን 2021/22 የዉጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ክፍያ መወሰን እና ማፅደቅ፤
 9. የመደበኛ ጉባዔዉን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ ናቸዉ፡፡

የ10ኛ አስቸኳይ/ድንገተኛ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. ምልዓተ-ጉባዔ መሙላቱን ማረጋገጥ፣
 2. የጉባዔዉን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 3. የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ስለማሻሻል፤ እና
 4. የአስቸኳይ/ድንገተኛ ጉባዔዉን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ ናቸዉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- በስብሰባዉ ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከስብሰባዉ ዕለት ቢያንስ አንድ ቀን በፊት አክሲዮን ማህበሩ ለዚሁ ዓላማ ያዘጋጀዉን የዉክልና መስጫ ቅጽ ማህበሩ ዋና መ/ቤት ድረስ በአካል ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰዉ መወከል ይችላል፡፡

የዲሬክተሮች ቦርድ

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ.