ቡና ባንክ አ.ማ ሲገለገልባቸው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 10/10/2022
- Phone Number : 0111580879
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/22/2022
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BB/PFMD/004/2022
ቡና ባንክ አ.ማ ሲገለገልባቸው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሸከርካሪው አይነት | የምርት ዘመን | የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር (ከተ.እ.ታ በፊት) |
1 | 3-A69204 | ሃዩንዳይ ክሬታ | 2018 | 2,304,348.00 |
2 | 3-A69226 | ሃዩንዳይ ክሬታ | 2018 | 2,304,348.00 |
3 | 3-A69240 | ሃዩንዳይ ክሬታ | 2019 | 2,434,783.00 |
የጨረታው መመሪያዎች
- ተሸከርካሪዎቹን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቡና ባንክ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ዘውትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2015 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡20 ሰዓት የጨረታ ሰነድ በገዙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻውን አስር በመቶ(10%) በቡና ባንክ አ.ማ ወይም “Bunna Bank S.C” ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸውን ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተሸከርካሪዎቹን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አድራሻ መመልከት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ/ዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15% ይከፍላል፤ እንዲሁም ተጫራቾች ባሸነፉበት ዋጋ እና መንገድ ትራንስፖርት በሚገምተው የተሸከርካሪዎቹ ዋጋ ልዩነት ምክንያት የሚኖር የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ገዥ ይከፍላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 011-1-58-08-79/011-1-26-19-01
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!