ቡና ባንክ አ.ማ ሲገለገልባቸው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ያላቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Foreclosure
- Posted Date : 01/21/2023
- Phone Number : 0111580879
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/03/2023
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪች ለመሸጥ በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BB/PFMD/01/2023
ቡና ባንክ አ.ማ ሲገለገልባቸው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ያላቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሽከርካሪው ዓይነት | የምርት ዘመን |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
1 | AA-3-54459 | Chevrolet Aveo | 10-Oct-09 | 270,000.00 |
2 | AA-3-66470 | Hyundai i10 | 23-Dec-10 | 200,000.00 |
3 | AA-3-66462 | Hyundai i10 | 23-Dec-10 | 220,000.00 |
4 | AA-3-96601 | Renault Duster | 10-Nov-13 | 420,000.00 |
5 | AA-3-96248 | Renault Duster | 10-Nov-13 | 420,000.00 |
6 | AA 3-90573 | Nissan Pick-up | 30-Jul-13 | 950,000.00 |
7 | AA-3-A15270 | Toyota Avanza | 24-Apr-15 | 600,000.00 |
8 | AA-3A-25903 | Hyundai Grand i10 | 20-Nov-15 | 900,000.00 |
9 | AA-3A-25909 | Hyundai Grand i10 | 20-Nov-15 | 900,000.00 |
10 | AA-3A-25921 | Hyundai Grand i10 | 20-Nov-15 | 900,000.00 |
11 | AA-3A-25922 | Hyundai Grand i10 | 20-Nov-15 | 900.000.00 |
12 | AA-3A-25095 | Hyundai Grand i10 | 20-Nov-15 | 900,000.00 |
13 | AA-3A-54680 | Hyundai Grand i10 | 22-Mar-18 | 1,250,000.00 |
14 | AA-3A-56355 | Hyundai Grand i10 | 22-Mar-18 | 1,250,000.00 |
የጨረታው መመሪያዎች
- ተሸከርካሪዎቹን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቡና ባንክ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ጥር 26 ቀን 2015 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡20 ሰዓት የጨረታ ሰነድ በገዙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻውን አስር በመቶ(10%) በቡና ባንክ አ.ማ ወይም “Bunna Bank S.C” ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸውን ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተሸከርካሪዎቹን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አድራሻ መመልከት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ/ዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15% ይከፍላል፤ እንዲሁም ተጫራቾች ባሸነፉበት ዋጋ እና መንገድ ትራንስፖርት በሚገምተው የተሸከርካሪዎቹ ዋጋ ልዩነት ምክንያት የሚኖር የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ገዥ ይከፍላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን “CPO” ውጤቱ ከተገለፀ ከ 5 /አምስት/ ቀናት በኋላ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 011-158-08-79/0111261901
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!