ቡና ባንክ አ.ማ አገልግሎት የሰጡ የተለያዬ ብረታብረቶችን እና የጥበቃ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Bunna-International-Bank-Logo-reportertenders-4

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 10/29/2022
 • Phone Number : 0111580879
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/12/2022

Description

                   የተለያዩ ብረታብረቶችን ለመሸጥ የወጣ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BB/PFMD/05/2022

ቡና ባንክ አ.ማ አገልግሎት የሰጡ የተለያዬ ብረታብረቶችን እና የጥበቃ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት መለኪያ የጨረታ መነሻ ዋጋ ለአንድ ኪሎግራም (ከተ.እታ በፊት )
1 የተለያዩ ብረታብረቶች እና ያገለገሉ የጥበቃ ቤቶች በኪሎ ብር 32

 

 • ንብረቶቹን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን 2015 ዓ.ም በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ብር 100.00 (አንድ መቶ) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን ለተጠቀሰው ንብረት በኪሎ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ህዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ህዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡20 ሰዓት ሰነድ በገዙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
 • ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 20‚000.00 (ሃያ ሺህ) በቡና ባንክ አ.ማ ወይም “Bunna Bank S.C” ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ንብረቶቹን መመልከት የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ ሠነዱ ላይ ባለው መርሃ ግብር መሠረት መመልከት ይችላሉ፡፡
 • ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑና ከታክስ ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎች የጨረታ አሸናፊ ይከፍላል፡፡
 • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን በሙሉ ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
 1. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 ቡና ባንክ አ.ማ

የባለራዕዮች ባንክ!!

0111580879/0111261901