ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች(furnitures)፣የተለያዩ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎች፣ ደረሰኞች እና ቅጾች (Printing Documents)፣እና የፅህፈት መሳሪያዎች(Stationary) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Bunna-Insurance-S.C-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 09/13/2022
 • Phone Number : 0111263103
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/03/2022

Description

ቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የ ጨ ረ ታ ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች(furnitures)፣የተለያዩ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎች፣ ደረሰኞች እና ቅጾች (Printing Documents)፣እና የፅህፈት መሳሪያዎች(Stationary) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት የጨረታ ሰነዱ በየዓይነታቸው ማለትም፡-

S.N Description Remark
1 Furniture Items Lot (ጥቅል) 1
  2 Printing and stationary Items Lot (ጥቅል) 3
 1. የተዘጋጀ ሲሆን፡-
 1. እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በሎት ከተከፋፈሉት ዝርዝሮች ውስጥ በነጠላ ወይም በሁለቱም Lot (ጥቅል) መወዳደር ይችላል፡፡
 2. ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በእያንዳንዱ Lot (ጥቅል) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በኩባንያችን ስም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ጋራንቲ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው መጠን በታች ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል፡፡
 4. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳር ቤት ከአፍሪካ ሕብረት ጀርባ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ህንፃ ፋሲሊቲና ግዢ ዋና ክፍል (ምድር ቤት) በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም 6:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዐት በ8:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ምድር ቤት) ይከፈታል፡፡
 7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-31-03 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-      ቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት

            ፋሲሊቲና ግዢ ዋና ክፍል

            የስልክ ቁጥር፡- 011-126 – 31 – 03

አዲስ አበባ