ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ለመጪው አደሰ ዓመት የጠረጲዛ የቀን መቁጠሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Bunna-Insurance-S.C-logo-1

Overview

 • Category : Packaging & Papers
 • Posted Date : 04/16/2021
 • Phone Number : 0111263103
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/20/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂየ

ኩባንያችን ለመጪው አደሰ ዓመት የሚያገለግል ብዛት 2000 (ሁለት ሺ)የጠረጲዛ የቀን መቁጠሪያ (Table Calendar) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

 1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ላይ በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና ከፋይነት ማስረጃ ከታደሰ ታክስ ክሊራንስ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን ሰነድ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ድርስ በኩባንያው ዋና/መ/ቤት  ሳር ቤት ከአፍሪካ ህብረት ጀርባ ከርቸሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ቡና ኢንሹራንስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ የማይመለስ ብር 50 (አምሳ ብር) እየከፈሉ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
 3. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን ሰነድ ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ድርስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ በሚል ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች በሚገዙት ሰነድ ላይ በሰፈረው ዝርዝር መረጃ መሠረት ለእያንዳንዱ የሚጫረቱበትን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ በማካተት በግልፅ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት  ተዘግቶ  ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 7. ተጫራቾች ተጨማሪያ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 11-1-26 31 43 ወይም 251 11-1-26 31 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 8. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት (ሳር ቤት)

ፋሲሊቲና ግዥ ዋና ክፍል (ቤዝመንት)

የስልክ ቁጥር 011-1-26 31 03