ቢ ዲ አር  ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 06/01/2021
  • Phone Number : 0945555550
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/16/2021

Description

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ያገለገሉ ተሸርካሪዎች ጨረታ

ቢ ዲ አር  ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር  በአዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) በመወከል ባለቤትነታቸው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነርና የአለም ጤና ድርጅት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

የተሽከርካሪዎቹ ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቶች ከሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2013 እስከ እሮብ ሰኔ 9 ቀን 2013 /ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ኮተቤ 02 ቀበሌ ጎል ኢትዮጵያ አጠገብ በሚገኘው መጋዘን  ሲሆን ካለው የኮቪድ 19  ወረርሽኝ አንፃር  አስቀድሞ  በ0945555550  በመደወል ፕሮግራም አስይዞ መመልከትና መመዝገብ ይቻላል::

ለመጫረት ፍላጎት ያለው ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት ብር 300 በመክፈል መመዝገብና ለሚጫረባትቸው ለእያንዳንዱ የጨረታ መደብ ብር 200,000  (ሁለት  መቶ ሺ ብር)  ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ ፒ ኦ) በቢ ዲ አር  ኤም ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስም ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን እስቀድሞ ማስያዝና መጫረት ይኖርባቸዋል።

የጨረታው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ መኪና የሚሰጡት ዋጋ ከሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2013 እስከ እሮብ ሰኔ 9 ቀን 2013 /ም  ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::  የጨረታው ውጤት ለአሸናፊዎች  በሰጡት አድራሻ ይገለፅላቸዋል። በተጨማሪ ዝርዝር ውጤት በበሩ ላይ  ይለጠፋል:: ተሸናፊ ተወዳዳሪዎች ውጤት ከተገለፀ ቀን ጀምሮ ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

አሸናፊዎች  ለአሸነፉት ተሽከርካሪ ሙሉውን ክፍያ ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው እንስቶ ባሉ ቀጣይ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ሙሉን ክፊያ በቢ ዲ አር ኤም ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በዳሽን ባንክ በሚገኘው ሂሳብ ቁጥር 5254001764064 ቀሪውን ገንዘብ መክፈል ይኖርባቸዋል። ከፊል ክፍያዎች ተቀባይነት የላቸውም። በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መክፈል ያልቻሉ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ያጣሉ። ድርጅቱ ሌሎች አማራጮችን የመውሰድ መብቱ የተጠበቅ ነው።

ሁሉም ለጨረታ የቀረቡ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ሲገቡ ቀረጥ ያልተከፈልባቸው ናቸው በዚህ መሰረትም ተጫራቾች በኢትዮጵያ መንግስት ህግና ደንብ መሠረት ለመንግስት መከፈል ያለባቸው የግብር የታክስ ቀረጥ ግዴታዎች እና ስም ለማዘዋወር ይሁን የቦሎ ውዝፍና ሌሎች ክፍያዎች የገዢ ኃላፊነት መሆናቸው አውቆው መጫረት ይኖርባቸዋል::  እነዚህ ወጪዎች ከሽያጭ ዋጋ የማይቀነሱ ይሆናል።

ቢ ዲ አር  ኤም ትሬድንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር  ለተሸጡ ተሽከርካሪዎች ይሁን እቃዎች ምንም አይነት ሃላፊነት አይወስድም። ገዢዎች ለገዙዋቸው መኪኖችን አስፈላጊ ሰነዶችን ከተረከቡ በኃላ በ30 ቀናት ውስጥ አስፈላጊው የግብር የታክስ የቀረጥ ግዴታዎች እና ተያያዥ ወጪዎች ከፍለው በስማቸው አዘዋውሮ  መውሰድ ይኖርባቸዋል። በተቀመጠው  ግዜ  ገደብ  ያሸነፉዋቸው ተሽከርካሪዎች/እቃዎች የማያነሱ አሸናፊዎች በቀን ብር 300 ለመጋዘንና ጥበቃ ተጨማሪ ክፊያ ይዳረጋሉ

ሁሉም ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ  እንዲሁም በማይመለስ መልኩ ይሸጣሉ። ድርጅቱ ከላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ሳያሟሉ ወይም ለቀረበው የጨረታ መደብ ተመጣጣኝ ዋጋ አልተሰጠም ብሎ ካመነ ከተጫራቶች የተሰጠው ዋጋ ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ያሸነፏቸው መኪና/ኖችና ሲያነሱ የግል መጓጓዣ ማቅረብ አለባቸው

/ቤቱ  የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ 0945555550 ይደውሉ

Send me an email when this category has been updated