ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥር 898፣ 899 የቦታው ስፋት 1311 ካሬ ሜትር ፣ ጎጃም በረንዳ ጅንአድ አካባቢግራውንዱና ግቢው ከ10 ተሸከርካሪዎች በላይ ማቆም የሚችል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 09/24/2022
  • Phone Number : 0115571703
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/14/2022

Description

የህንፃ ኪራይ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/15

ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥር 898፣ 899 የቦታው ስፋት 1311 ካሬ ሜትር ፣ ጎጃም በረንዳ ጅንአድ አካባቢ ወረዳ 2 ጽ/ቤት አጠገብ ከዋናው መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኘውን በ600 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ ግራውንድ ሚዛኔና በሁለት ወለሎች ላይ የሚገኙ የተለያየ ስፋት ያላቸው  23 ክፍሎችን የያዘ ለቢሮ፣ ለክሊኒክ፣ ለላቦራቶሪ ስራ፣ ለስልጠና ማዕከልነት እና መሰል አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል፣ ግራውንዱና ግቢው ከ10 ተሸከርካሪዎች በላይ ማቆም የሚችል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ይህንኑ ህንፃ ለመከራየት የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ሙሉ ህንፃውን ለመከራየት የምትፈልጉበትን ቫትን ያካተተ ወርሃዊ ኪራይ ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ካዛንቺስ፣ ዘመን ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው ነጋ ሲቲ ሞል ስምንተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፣

ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  • ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ሲገለጽላቸው የ6 ወራት ኪራይ በቅድሚያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፣
  • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-5571703 መጠቀም ይችላሉ፡፡

ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል ማህበር