ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ይሸጣል፡፡

NICE-–-National-Insurance-Company-of-Ethiopia-s.c-logo-reportertenders

Overview

  • Category : Vehicle Foreclosure
  • Posted Date : 04/18/2021
  • Phone Number : 0114661129
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/29/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 4/2020/21)   

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ይሸጣል፡፡

ተጫራቾች ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. 4፡0ዐ  ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ  ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ንብረቶቹንከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. 4፡0ዐ  ሰዓት ድረስ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፡፡

የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ቫት ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫት ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት  በ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ወይም በእንግሊዝኛ NATIONAL INSURANCE CO. OF ETHIOPIA (S.C.) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. 4፡0ዐ  ሰዓት ላንቻ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ውል ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡0ዐ ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት በ4፡30 ሰዓት ላይ በኩባንያው ንብረት ማከማቻ ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡:

ማሳሰቢያ፡አሸናፊ ተጫራቾች ለአሸነፉት ንብረት ክፍያ ሲፈፅሙ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ባቀረቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨምሩ መሆኑን እንገልፃለን፡:

ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል፡፡ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ8 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ካልተረከቡ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡  የተሽከርካሪው የስም ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ከቀረጥ ነፃ የገባ ተሽከርካሪ ለአሸናፊው ተጫራች የምናስረክበው የጉምሩክ ቀረጥ ከፍሎ ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ነው፡፡ ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ስልክ 011-466-11-29/0114-65-56-05