ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Berhan-International-Bank-S.c-logo-2-4

Overview

 • Category : Office Items & Equipment sale
 • Posted Date : 07/24/2021
 • Phone Number : 0116631729
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/17/2021

Description

ብርሃን ባንክ አ.ማ.

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ጠ/አ-01/14

ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ.

ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶች ዝርዝር

 
 

1

ያገለገሉ ጀነሬተሮች

 

2

ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች (office equipment)

 

3

ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች (office furniture)

 

4

ያገለገሉ የሞተር ሳይክል ጎማዎች

 
 1. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ንብረቶች ዝርዝር፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ እና የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ ንብረቶቹን ገርጂ ኢምፔሪያል ሆቴል አለፍ ብሎ በሚገኘዉ ኖክ ነዳጅ ማደያ አጠገብ ባለዉ ስፓልት መንገድ 300 መቶ ሜትር ወደ ዉስጥ ገብተዉ ከ40/60 ኮንዶሚንየም ፊት ለፊት በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን ቅጥር ጊቢ እና ቃሊቲ በሸዋ ዳቦ መጋገሪያ ፋብሪካ ወደ ዉስጥ ገብተዉ የሚድሮክ ማሽነሪ ጋራዥ ፊት ለፊት በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ንብረት የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በC.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች በዝርዝር የተጠቀሱትን ንብረቶች አጠቃለዉ ወይም በተናጠል መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት አስከ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ከላይ በ2ተኛ ተ.ቁ. በተጠቀሰዉ አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታዉ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ያገለገሉ ንብረት ባቀረቡት ነጠላ ዋጋ መሰረት በአጠቃላይ ብዛቱ ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋዉን በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአምስት ቀን ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡

ተጫማሪ መረጃ ከፈልጉ በስልክ ቁጥር 0116631729 /0116395175 /0116182624/ ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ /ብርሃን ባንክ አ.ማ./