ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላለው ቀጣይ የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶችን፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞችን (ቶነሮች) ፣ የአይሲቲ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች በተጨማሪም ለዚሁ ዓመት የሚሆን የሰራተኞች የደንብ ልብስ ከታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Berhan-Insurance-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 08/06/2022
 • Phone Number : 0114674423
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/17/2022

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላለው ቀጣይ የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶችን፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞችን (ቶነሮች) ፣ የአይሲቲ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች በተጨማሪም ለዚሁ ዓመት የሚሆን የሰራተኞች የደንብ ልብስ ከታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ምድብ አንድ፡- የፅህፈት መሳሪያዎች

ምድብ ሁለት፡- የህትመት ውጤቶች

ምድብ ሶስት፡- የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞት (ቶነሮች)

ምድብ አራት፡- ኢንቨርተር ከነባትሪው

ምድብ አምስት፡- የሰራተኞች የደንብ ልብስ

ምድብ ስድስት፡- የፅዳት ዕቃዎች

በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለሚፈልጉት ምድብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ በኩባንያው ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 4. ጨረታ ሰነዱን በፓስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ተገኝተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ለተወዳደረበት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶችን፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞችን (ቶነሮች)፣ የአይሲቲ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ነሃሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡3ዐ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት

ወሎ ሰፈር ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7

የሠው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ

ስልክ 0114674423/46 ወይም 0114704054