ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ

Berhan-Insurance-logo-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/19/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/17/2022

Description

   የማህበሩ ዋና ገንዘብ/ካፒታል/= 220,000,000

 የምዝገባ ቁጥር= MT/AA/2/0011599/2004

 ለብርሃን ኢንሹራንስ  ባለአክስዮኖች  የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ

ብርሃን  ኢንሹራንስ  አ.ማ. የባለአክሲዮኖች  11ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ   ቅዳሜ  ታህሣሥ 8  ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት  ጀምሮ  አዲስ አበባ፤ ካዛንቺስ  በሚገኘው  ኢሊሊ ሆቴል ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያችን ባለአክሲዮኖች በሙሉ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፍቃድ/ፓስፖርት  በመያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ሀ. የመደበኛ ጉባኤ አጀንዳ

 1. አጀንዳውን ማጽደቅ፤
 2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ
 3. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ 2021/22 ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ
 4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ 2021/22 የሂሳብ ሪፖርት ማድመጥ
 5. ከዚህ በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴን ሪፖርት መስማትና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፤
 7. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን
 9. የውጭ ኦዲተሮች መሰየምና ክፍያቸውን መወሰን
 10. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ለ. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

 1. አጀንዳውን ማጽደቅ፤
 2. የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ
 3. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ 

በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ፡-

 • ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን  አስቀድሞ  ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ  7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ በመሙላት ተወካይ በመወከል ወይም
 • በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ በጉባኤው እለት ይዞ በመቅረብ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ብርሃን ኢንሹራንስ .

የዳይሬክተሮች ቦርድ