ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን በዕውቅ ባለሙያዎች ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Berhan-Insurance-logo

Overview

 • Category : Bank Related
 • Phone Number : 114674430
 • Source : Reporter
 • Posted Date : 03/22/2023
 • Closing Date : 04/05/2023

Description

የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስመ ጥር እና ታዋቂ በሆኑ ኢትዮÉያውያን ባለሃብቶች እና ድርጅቶች በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም. ተመስርቶ ለህብረተሰቡ ህይወት ነክ ያልሆነ የኢንሹራንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በዘርፉ በቂ እውቀትና ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች በመቅጠር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና አስተማማኝ የሆነ የኢንሹራንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ኩባንያውን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን በዕውቅ ባለሙያዎች ለማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በዝርዝር በቀረቡት መስፈርቶች መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች እና ባለሙያዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

 1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎሰፈር አደባባይ፣ ጋራድ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ላይ በሚገኘው የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት 7ተኛ ፎቅ የሰው ሃብት እና ንብረት አስተዳደር በመገኘት እስከ መጋቢት 28፣ ቀን 2015 ዓ.ም የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ስም አዘጋጅተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ተተይቦ ወይም በጉልህ የእጅ ጽሁፍ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 5. የጨረታ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን (የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዱን ያካተተ) እስከ መጋቢት 28፣ ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው መጋቢት 28፣ ቀን 2015 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት 7ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት

ወሎሰፈር አደባባይ፣ ጋራድ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 7ተኛ ፎቅ

ስልክ: 0114-674431 / 0114-674423/46

ፋክስ: 0114-668701

ዌብሳይት: www.berhaninsurance.com

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ