ብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Nib-International-Bank-logo-2

Overview

 • Category : Spare Parts Sale & Supply
 • Posted Date : 04/17/2022
 • Phone Number : 0115512650
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/10/2022

Description

ያገለገሉ እቃዎች የሽያጭ ጨረታ  

የጨረታ መለያ ቁጥር  ንብ/35/2014

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ  ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የእቃዎች ዝርዝር መግለጫ መለኪያ ብዛት
1 ያገለገሉ ጀነሬተሮች እና ባትሪዎች በቁጥር የተለያዩ አይነት
2 ያገለገሉ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ›› የተለያዩ አይነት
3 ያገለገሉ የተለያዩ የሻይ ቤት እቃዎች ›› የተለያዩ አይነት
 1. ጨረታው በባንኩ የግዢ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሂደት መሰረት ይከናወናል፡፡
 2. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሠርቲፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00/ብር አንድ መቶ/ በመክፈል ከሚያዝያ 12, ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ኢምፔሪያል ሆቴል ጀርባ ከሜዲቴክ አጠገብ በሚገኘው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ማዕከላዊ መጋዘን በመገኘት ከላይ የተጠቀሱትን ያገለገሉ ዕቃዎች በመጎብኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቶች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 6 ስር በተጠቀሰው አድራሻ እስከ ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም. 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ለባቸው፡፡ ዘግይቶ የደረሰ መወዳደሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ብር ሀያ አምስት ሺህ ) ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ባላካተተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ጨረታው ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ግንቦት 02  ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 9፡15 ሰዓት ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ  26ኛ ፎቅ ግዢ ዋና ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡
 7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911092225/0116296246/0115504452 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ስልክ ቁጥር  0115512650/0115504452

ፋክስ  011 5 622448