ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል ለሚያስተምራቸው ተማሪዎቹ ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Hope-Enterprises-Logo-1

Overview

  • Category : Catering Service
  • Posted Date : 08/24/2021
  • Phone Number : 0118723619
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/09/2021

Description

የምግብ አቅርቦት የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት ፣ በሙያ ስልጠና እና በእለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል ለሚያስተምራቸው ተማሪዎቹ

  1. በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ነገሌ በራፉ ሀርጌሳ ሮጌ ቀበሌ ለሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 700 ተማሪዎች
  2. በኦሮሚያ ክልል በዝዋይ ዱግዳ ሂራራ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 600 ተማሪዎች
  3. በሲዳማ ክልል በመልጋ ወረዳ በሲንታሮ ቀበሌ ለሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 500 ተማሪዎች

ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቅጽ/ሰነድ ከተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት ወይም ከየፕሮጀክቶቹ በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ Ôጉሜ 3 ቀን 2013፣ ከቀኑ 10.00 ሰአት ድረስ መውሰድ እና መወዳደር እንደምትችሉ እናስታውቃለን፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሚከተለው አድራሻ ማስገባት/ መላክ ይኖርባቸዋል

  • ተስፋ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት አ.አ (አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊትለፊት) የመልዕክት ሳ.ቁ 30153 ወይም በግንባር በመገኘት ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው  Ôጉሜ 4 ቀን 2013 ከቀኑ ከጠዋቱ 4.00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራጮች ለአንድ የትምህርት አመት ባቀረቡት ዋጋ ምግቡን የማቅረብ ሀላፊነት አለባቸው፡፡

ለተጨማሪ አድራሻ፡- ስልክ ቁጥር 0118723619