ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅትበዘዋይ ዱግዳ ወረዳ ሂራራ ቀበሌ ለሚገኘው ኘሮጀክት ዳረጃውን የጠበቀ የኮንክሪት የውሃ ታንከር ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

Hope-Enterprises-Logo-1

Overview

 • Category : Water Well Drilling & Water System Installation
 • Posted Date : 11/21/2022
 • Phone Number : 0113694480
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/02/2022

Description

የውሃ ታንከር ግንባታ ስራ  ጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ሲዳማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት ፣ በሙያ ስልጠና እና በእለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ስለሆነም በኦሮሚያ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት በዘዋይ ዱግዳ ወረዳ ሂራራ ቀበሌ ለሚገኘው ኘሮጀክት ዳረጃውን የጠበቀ የኮንክሪት የውሃ ታንከር ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራÓች፡-

 1. ደረጃቸው GC/WWC Grade 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡ የ2015 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከህዳር 12, 2015 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከድርጅቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ በድርጅቱ ስም ማሳራት አለባቸው፡፡
 4. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለ{ለት የመልካም ስራ አፈፃፀም (Performance bond) የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና በማያያዝ ውል ይፈራረማል፡፡
 5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ መሰረት ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፐ አድርገው እስከ ህዳር 22, 2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ጨረታው ህዳር 23, 2015 ዓ.ም ከቀኑ 4.00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሠብሠቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ፡-    ተስፋ ድርጅት  ዋና መ/ቤት

አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት

ፖ.ስ.ቁ ፡ 30153

ስልክ ቁጥር 0113694480

አዲስ አበባ