ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ከውጪ ያስመጣቸውን አገልግሎትያልሰጡና ለረዥም ጊዜ የቆዩ የወጥ ቤት ዕቃዎች እና አሮጌ የሆስፒታል አልጋዎች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 11/07/2022
  • Phone Number : 0911406042
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/04/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

አድራሻ፡-አዲስ አበባ ክ/ከተማ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 09

ከጦርሀይሎች ዝቅ ብሎ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ

  1. ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ከውጪ ያስመጣቸውን አገልግሎትያልሰጡና ለረዥም ጊዜ የቆዩ የወጥ ቤት ዕቃዎች እና አሮጌ የሆስፒታል አልጋዎች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡

ተጫራቾች በሆስፒታሉ በመገኘት እቃዎቹን በማየት የጨረታ ሠነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

ተጫራቾች፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ንብረቶች በሚገኙበት አድራሻ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት በመመልከት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣበት ቀን 25/02/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  3. ሆስፒታሉ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ለተጫራቶች ምንም ኃላፊነት ሳይኖርበት ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ሲያስፈልግዎ 0911406042 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር