ታምሪን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር 13 ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 07/27/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/10/2022

Description

ታምሪን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር 13 ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

 1. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት መግዛት ይኖርባቸዋል፤
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከዘጠነኛው ቀን ጀምሮ ጨረታው አስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖረባቸዋል፤
 3. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፤
 4. የሚሸጡት መኪኖች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን በዘጠነኛው እና በአስረኛው ቀን በድርጅቱ ዋና መስሪያቤት የጨረታ ሰነድ ለገዙ ተጫራቾች ብቻ ለእይታ ዝግጁ ሆነው ይቀመጣሉ፤
 5. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ላይ ተዘግቶ በዚያው እለት ከረፋዱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን፤የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል፤
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት
 7. ተጫራቾች መኪናውን /መኪኖችን ለመግዛት ከሚያቀርቡት ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) በሲፒኦ (CPO ) የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
 8. የሚሸጡት መኪኖች ዓይነትና ሞዴል ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጸዋለ፤
 9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው ሰንጠረዥ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ሊገዙት በሚፈልጉት መኪና ትይዩ ባለው የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
 10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡