ታቦር የሴራሚክስ ውጤቶች አ.ማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትንና በድርጅቱ መጋዘኖች ውስጥ የሚገኙትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 01/23/2023
  • Phone Number : 0911952079
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/28/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 

ድርጅታችን ታቦር የሴራሚክስ ውጤቶች አ.ማ ከዚህ በታች የተጠቀሱትንና  በድርጅቱ መጋዘኖች ውስጥ የሚገኙትን ዕቃዎች በጨረታ  አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡

1ኛ/ የባኞ ቤት ዕቃዎች(የእጅ መታጠቢያ ከነ ማቆሚያው፤የሽንት ቤት መቀመጫ ከነ ሙሉ ዕቃው፤ተርኪሽ በተለያየ ከለሮች እና የሶፍት የሳሙና ማስቀመጫ ወዘተ…)

2ኛ/ የማዕድ ቤት መገልገያዎች (ድስቶች፤ሳህኖች፤የወተት፤የቡና፤የማኪያቶ እና የሾርባ መጠጫ ማጎች፤የሻይ እና የወተት ማፍያ እና ማቅረቢያዎች የቡና ማፍያ ጀበናዎች እስከነ ሲኒያቸው ወዘተ…..)

3ኛ/ የሳሎንና ቢሮ ማስጌጫዎች (የተለያ ቀለም እና ጌጥ ያላቸው የአበባ ማስቀመጫዎች)

4ኛ/ የተለያየ ቀለም ያላቸው የግድግዳ እና የወለል ንጣፍ ሴራሚኮች (15*15፤15*20፤30*30፤20*30 ወዘተ…) ከላይ የተገለፁትን ዕቃዎች

ለጨረታ ያቀረብን ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ጉርድ ሾላ ፒካን ህንፃ ኢትዮ ሴራሚክ ከሚገኝበት ህንጻ ጎን 2ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድ እና ዕቃዎቹንም በአካል ማየትና መሳተፍ ይችላሉ ፡፡

ማሳሰቢያ

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች

1ኛ/ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው

2ኛ/ ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃ ከአጠቃላይ ዋጋ ላይ አምስት በመቶ          (5 ፐርሰንት) በባንክ ማዘዣ(ሲፒኦ) አሰርተው ከዋጋ መቅረቢያው ጋር አያይዞ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል

2ኛ/ የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ከፍለው ዕቃ በ 15  (በአስራ አምስት) ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ማንሳት ይኖርባቸዋል ፡፡

3ኛ/ ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች በአንድ ሳምንት ውስጥ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ፡፡

4ኛ/ ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ጥር 20/2015 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡

5ኛ/ ጨረታው ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን በገዛችሁበት ቦታ በ22/5/2015 ልክ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ፡፡

6ኛ/ ድርጅታችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 0911952079/ መደወል ይችላሉ ፡፡