ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ እንተሪየር ዲዛይን አሰርቶ በዲዛይኑ መሰረት የማጠናቀቂያ ስራዎችን በመጨረስና የቤት እቃዎችን በማስገባት ለገዥዎች የቤቶችን አቅምና ውበት በተግባር የማሳያ ቤት አድርጎ ማዘጋጀት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo

Overview

  • Category : Architects Service
  • Posted Date : 09/10/2021
  • Phone Number : 0913098889
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/24/2021

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

በትራኮን ሪል ስቴት አንድ የሳምፕል ቤት የኢንተሪየር ዲዛይነር/INTERIOR DESGINER/ ለማሰራት የወጣ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ በሚገኘው ትራኮን ሪል ስቴት 3B+G+22 የአፓርታማ ህንጻዎች ግንባታ እያከናወነ አሁን ወደ ማጠናቀቂያ ስራዎች እየገባ ይገኛል፡፡

እነዚህ የአፓርታማ ቤቶች ወደ ማጠናቀቂያ/finishing/ሥራ እየሄዱ ስለሆነ፤አንድ ቤት በናሙናነት/sample house/እንተሪየር ዲዛይን አሰርቶ በዲዛይኑ መሰረት የማጠናቀቂያ ስራዎችን በመጨረስና የቤት እቃዎችን በማስገባት ለገዥዎች የቤቶችን አቅምና ውበት በተግባር የማሳያ ቤት አድርጎ ማዘጋጀት ይፈልጋል፡፡

ይህንን የናሙና ቤት/sample house/ አራት መኝታ ቤት ያለው 237 ካ.ሜ ስፋት ላይ ያረፈ ኢንተሪየር ዲዛይን በማሰራት ለማስዋብ፤በስራው ላይ ልምድ ያላቸውን የኢንተሪየር ዲዛይን ባለሙያዎች/ድርጅቶች ዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል ፡፡በዚህ ማስታወቂያ ተመርጦ ተስማምቶ የሚገባ ባለሙያ/ድርጅት ከባለቤት ኩባንያው ጋር ቀጣይ መልካም የሥራ ግንኙነት ከመፍጠሩ በተጨማሪ፤የተጠናቀቀውን ቤት ከሚጎበኙና ከሚገዙ ባለሀብቶች ጋር በማስታወቂያነት/promotion/ ተጠቃሚ ያደርገዋል፡፡

ስለዚህ ተወዳደሪዎች የአፓርታማ ህንጻዎቹን እና የተመረጠውን የሳምፕል ቤት በአካል በማየት፤የስራ ልምዳቸውን እና ለስራው የሚጠይቁትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማመልከት ይችላሉ፡፡

ተወዳደሪዎች የሚያስገቡት ዋጋ የዲዛይን እና የማማከር ሲሆን ባለቤት ኩባንያችን ማቴሪያሎችን የሚያቀርብ በመሆኑ፤ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ማቴሪያል አቅራቢዎችን የእጅ ስራ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በመጠቆምና በማገናኘት እንዲሁም የሥራውን ጥራት የመቆጣጠር የስራ ድርሻዎች እንደሚካተቱ ከግምት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

አመልካቾች  የ2013 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ  –   ስልክ፡-0913098889/0989098625