ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሳኒቴሪ እቃዎችን በዘርፉ ልምድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0930013343
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/25/2022

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር የሳኒቴሪ ዕቃዎች ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 2061/2015

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሳኒቴሪ እቃዎችን በዘርፉ ልምድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልታችሁ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 1. ተጫራቾች የ2015 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ሰርተፍኬት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ለሰጡት ተመሳሰይ አገልግሎት መልካም ስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች በተያያዘው የዕቃዎቹ ሊስት መሠረት ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 በተጠቀሱት እያንዳንዱ ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ መጠቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች የሚያስረክቡበትን ጊዜ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ መሙላት አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላውን 2 (ሁለት ከመቶ) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የጨረታውን ዶክሜንት ከትራኮን ታወር ዜሮ ወለል ህዳር 05 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ብር 100 በመክፈል መውሰድ የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ እስከ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለዚሁ በተዘገጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 7. ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 በትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ በድርጅቱ ቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡
 8. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ሊሆኑ እና የጥራት ዋስትና የመስጠት እንዲሁም ከደረጃ በታች የሆኑ እቃዎችን የመመለስ ወይም የመቀየር ግዴታ አለባቸው፡፡
 9. ተጫራቾች ለሁሉም እቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ፓ.ሣ.ቁ 2243 ኮድ 1250

ሞባይል 0930013343/0921338558