ትራኮን ትሬድንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሪል ስቴት ዘርፍ አሁን እየገነባ ለሚገኘው ወደ ማጠናቀቂያ ደረጃ እየደረሰ ላለው በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ ለሚገኘው 3B+G+22 እና የአፓርታማ ህንጻዎች/አራት ታወሮች/የሴንትራል ቴሌቪዥን ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo-4

Overview

  • Category : Entertainment & Docu
  • Posted Date : 08/28/2021
  • Phone Number : 0913098889
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/08/2021

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

የሴንትራል ቴሌቪዥን የማማከርና የገጠማ ስራ/CENTRAL TV SYSTEM/ለማሰራት የወጣ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ትራኮን ትሬድንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሪል ስቴት ዘርፍ አሁን እየገነባ ለሚገኘው ወደ ማጠናቀቂያ ደረጃ እየደረሰ ላለው በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ ለሚገኘው 3B+G+22 እና የአፓርታማ ህንጻዎች/አራት ታወሮች/የሴንትራል ቴሌቪዥን ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በሴንትራል ቴሌቪዥን ስራ እውቀቱና በፕሮጀክታችን ደረጃ ያለ ስራ በመስራት ልምዱ ያላችሁ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች የፕሮጀክቱን ፍላጎት በአካል ፕሮጀክቱን በመጎብኘት እና መሀንዲሶችን በማማከር መረጃ በመውሰድ ለፕሮጀክቱ የምትጠቀሙትን ስፔስፊኬሽን እና ዋጋ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የሴንትራል ቴሌቪዥን ስፔስፊኬሽን መስራት፤ቀጣሪ ድርጅቱን በማማከር ለስራው የሚፈልጉ ማቴሪያሎችን ቀጣሪ ድርጅቱ እንዲያቀርብ የማድረግና ገጠማውን የማከናወን የስራ ድርሻ የሚኖራቸው ሲሆን፤የሚቀርቡት ዋጋም ይህን ያገናዘበ  እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

በፕሮጀክቱ ባሉት አራት የአፓርታማ ህንጻዎች ውስጥ ጠቅላላ 356 አባወራ ቤቶች የሚኖሩ ሲሆን፤ለአንድ ቤት 2/ሁለት/ የቴሌቪዥን ቀጥታ መስመር ሲታሰብ 712 TV points ይኖራሉ፡፡

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በወጣ በተከታታይ ባሉ 10 ቀናቶች ውስጥ ለቴክኒካል ውድድር የሚሆናችሁን ካምፓኒ ፕሮፋይል እና ስራውን የምትሰሩበትን ዝርዝር ስፔሲፍኬሽን በአንድ የታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲሁም የምታቀርቡትን ዝርዝር እና ጠቅላላ ዋጋ በተለየ ኢንቨሎፕ በማድረግ በማስገባት እንዲትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ዝቅተኛ መመዘኛ እንዲያሟሉ ይጠበቃል፡፡

  • በሴንትራል ቴሌቪዥን ስራ ላይ ቢያንስ 5 አመት ስለመስራቱ እና የሰራቸውን ስራዎች ያካተተ ካምፓኒ ፕሮፋይል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ከቴክኒካል እና ፋይናንሻያል በተጨማሪ ስራውን ለማጠናቅቅ የሚወስድበትን የጊዜ መጠን መግለፅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • በ2013 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ሆነው ሰርትፊኬት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ

ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ

ሞባይል ፡0913098889/09 89 09 86 25