ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ኩባንያው ባቀረበው ዲዛይን መሰረት ለነዳጅ ማደያ ካፌዎቹ መገልገያ የሚሆኑ የተለያየ አይነት ያላቸው ፈርኒቸሮችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Total-Energies-Marketing-Ethiopia-SC-logo-1

Overview

 • Category : Other Furniture
 • Posted Date : 01/18/2023
 • Phone Number : 00114653044
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/20/2023

Description

የነዳጅ ማደያ ካፌዎች መገልገያ ፈርኒቸሮች ጨረታ

 ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ኩባንያው ባቀረበው ዲዛይን መሰረት ለነዳጅ ማደያ ካፌዎቹ መገልገያ የሚሆኑ የተለያየ አይነት ያላቸው ፈርኒቸሮችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት መጫረት ይችላል፡፡

 1. ተጫራቾች የፈርኒቸሮችን ዝርዝር ዲዛይን የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም C.P.O. ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ P.O.  ተመላሽ ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት /15/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ጨረታው ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ተከፍቶ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ይዘጋል፡:
 5. ተጫራቾች በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT / መጨመር አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾቸ የጨረታውን ሰነድ በፖስታ አሽገው ፖስታው ላይ የጨረታውን ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን አንስቶ በ5 ቀን ውስጥ ሙሉውን ዋጋ ከፍሎ ዕቃውን ካላነሳ ያስያዘው ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
 8. ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ አ.ማ. የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 9. አድራሻ ከጎተራ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ላይ ቡና ቦርድ አካባቢ ሙለጌ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡

ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ.

ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል

ሳሪስ መንገድ ቡና ቦርድ ፣ ሙለጌ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ , 0114 65 3044 ወይም 011 466 8025