ቶታልኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ ለግለሰብ ኦኘሬተር /የሽያጭ ወኪል/ አወዳድሮ በውል መስጠት ይፈልጋል፡፡

Total-Energies-Marketing-Ethiopia-SC-logo-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/21/2022
 • Phone Number : 0114651125
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/02/2022

Description

የጨረማስወቂያ

ቶታልኢነርጂስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንጋፋ ከሆኑትና በነዳጅ፣ በተፈጥሮ ጋዝ እና በዝቅተኛ ካርቦን ኤሌክትሪሲቲ ሽያጭ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በዓለማችን በ13ዐ አገራት ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ቶታልኢነርጂስ በኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ. ከ195ዐ ዓ.ም. ጀምሮና ከ16 ዓመት በፊትም ከሞቢል ኢስት አፍሪካ ውህደት በጠቅላላው በመላው ሀገሪቱ ከ143 በላይ በሆኑ ነዳጅ ማደያዎችና 5 የነዳጅ ማከማቻ ዴፖዎች ሃላፊነት በተሞላው መንገድ የሽያጭ እና የአገልግሎት አሰጣጥን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በአንፃሩም ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. በሀገሪቱ ካሉት የነዳጅ ኩባንያዎች መሪ ከሆኑት ከዘርፉ ኩባንያዎች በነዳጅና በዘይት ሽያጭ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ብቸና ከተማ የሚገኘውን የብቸና ቶታልኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ ለግለሰብ ኦኘሬተር /የሽያጭ ወኪል/ አወዳድሮ በውል መስጠት ይፈልጋል፡፡

 • ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካች ግለሰቦች(
 1. በትምህርት ደረጃቸው ቢያንስ 1ዐኛ ክፍልን ያጠናቀቁና የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የነዳጅ ማደያው ሥራ የሚጠይቀውን የመሥሪያ ካፒታል /ገንዘብ/ በግላቸው የማቅረብ አቅም ያላቸው፣
 3. ወቅታዊ የሆነና ያለፉትን 6 ወራት የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ከባንኩ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት የሚችሉ፣
 4. የነዳጅ ማደያውን የዕለት ተዕለት ሥራ በቂ ጊዜ ሰጥተው በግላቸው መምራት የሚችሉና፣ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. አመልካቾች የብቸና ከተማ ወይንም አካባቢ ነዋሪ መሆን አለባቸው፣
 6. ጊዜው ያላለፈበትና ተቀባይነት ያለው መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ የሚችሉ፣
 7. የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ያለው/ያላት ወይም ለመግዛት የሚችሉ፣
 • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች(
 1. የማይመለስ ብር00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የማመልከቻ ሰነዱን ሙለጌ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው ዋና /ችን የሽያጭ ቢሮ ድረስ በመቅረብ ይህ ማስ(ወቂያ ከወጣበት መጀመሪያ ቀን ከሕዳር 12 ቀን 215 .ስከ ሕዳር 23 ቀን 215 . ከቀኑ 1000 /አስር ሰዓት/ ድረስ የጨረታ ሰነዱን ገዝተውና ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የማመልከቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 3. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ከማመልከቻ ሰነድዎ ጋር የሚከተሉት ደጋፊ መረጃዎች አባሪ መደረጋቸውን አይዘንጉ(
 1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፣
 2. ያለዎትን የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ ቢያንስ የ6 ወር ተቀማጭ/ተንቀሳቃሽ ሂሳብዎን የሚገልጽ የባንክ እስቴትመንትና የባንክ የማረጋገጫ ደብዳቤ፣
 3. የትምህርት ደረጃዎን የሚያሳይ የተሟላ የትምህርት መረጃ ፎቶ ኮፒ፣
 4. ያለዎትን ንብረት የገንዘብ አቅም ለማሳየት እንዲቻል ወቅታዊ የሆነ የቋሚ የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ /ካለ/፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥሮች – 011 465 11 25 / 011 465 45 25 ይጠይቁ፡፡

ቶ(ልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር