ቻሪቲ ኤንድ ዲቮሎፕሜንት አሶሴሽን አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ያገለግሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 09/09/2021
 • Phone Number : 0114716585
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/08/2021

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቻሪቲ ኤንድ ዲቮሎፕሜንት አሶሴሽን አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ያገለግሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተሸከረካሪዎች አጭር መግለጭ

ተ.ቁ  የተሸከርካሪው ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር
1 ቶዮታ  ላንድኩሩዘር  ሎንግ ቤዝ ዕድ-35-1132
2 ሃይሉክስ ሰርፍ  (Hilux surf) ዕድ-35-860
3 ሞተር ሣይክል ሊፋን ዕድ-35-1411

የተጫራቾች መመሪያ

 1. የአንድ ተሽከርካሪ ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር00/ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቢሮ ሕንፃ ጀርባ ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አለፍ ብሎ ከጥቃቅኖች ጎን ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ከሰው ኃይልና ፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ) ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በመግዛት ንብረቶቹንም በአከል መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከረካሪ ጠቅላላ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
 3. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት/15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት  የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ባዶ ቦታ የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፖስታ/ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጫረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 14ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-10፡00 ሰዓት እና በ15ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጫረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪውን ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 ቀናት ከፍለው በ10 ቀን ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
 7. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114716585/0911478954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡