ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ ጉዳት ደርሶባቸው ተሽከርካሪዎችን፤መለዋወጫዎችና ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 10/15/2022
- Phone Number : 0116626667
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/31/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር SD/48/22
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች ተገቢውን ካሣ ከከፈለ በኋላ የተረከባቸውን ቀረጥ የተከፈለባቸውና ያልተከፈለባቸው ተሽከርካሪዎችን፤መለዋወጫዎችና ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር መመሪያና ዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ከዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 307 የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ከፍለው በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የሚወዳደሩባቸውን ንብረቶች ዝርዝር በመግለጽ እእስከ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ጧት 4፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታታቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ ዐ4 ሚኪሊላንድ መንገድ በሚገኘው ፕሮቴክሽን ሀውስ ምድር ቤት ዋናው መግቢያ ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የሚገዙትን ዕቃ ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ ተጫራቾቹ ለመግዛት በኩባንያው መነሻ ዋጋ ላይ 10% የጨረታ ዋስትና ለኩባንያው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) አሠርተው ከጨረታው ሠነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት በኩባንያው የሠራተኞች ክበብ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡:
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ
የስልክ ቁጥር 011-6-626667