ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶች አምራች ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

National-Cement-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 09/26/2022
 • Phone Number : 0114401495
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/17/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶች አምራች ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ የእቃው አይነት መለኪያ ብዛት አይነት የአንዱ ዋጋ ከቫት

በፊት

1 የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢት (AD star WPP laminated cement bags) በቁጥር 12,000,000 ኦፒስ (OPC)  
ፒፒሲ(PPC  

በመሆኑም ተጫራቾች   

 • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 • የተዘጋጀውን የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶች ሰነድ (Specification & Art work) በቴሌግራም ቻናል nationalcementscBID (National Cement A.A Support Office) ያለምንም ክፍያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶችን የአንዱን ዋጋ በመሙላት እንዲሁም የማሸጊያ ከረጢቶችን ናሙና (sample) ለኦፒሲ (OPC) ብዛት 20 እና ለፒፒሲ (PPC) ብዛት 20 በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 251 11 4 401495 / 0960-36-71-36 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0935-98-50-83/0946-43-93-94 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ጨረታው ጥቅምት 3/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ጥቅምት 7/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 • ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
 • ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለ

ድርጅቱ!