ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ በማምረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ከታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

national-premix-construction-plc-logo

Overview

 • Category : Machinery Sale
 • Posted Date : 12/26/2022
 • Phone Number : 0118225392
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/09/2023

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ከናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ በማምረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ከታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ 1) ሚክሰር ትራክ

ተ.ቁ 2) ሃፍ ክሬን ትራክ

ተ.ቁ 3) ትራክ ማዉንትድ ፓምፕ

 1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ አቅራቢዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  • ከስራው ጋራ አግባብነት ያለው የ2015 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
  • የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  • የተፈረመ እና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድረጊት ላለመፈጸም ቃል የገባበት ቅጽ ማቅረብ የሚችል
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዳቸዉ የማይመለስ 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከ17/04/2015 ጀምሮ በስራ ሰዓት ዋና መስሪያ ቤት ሳር ቤት አካባቢ ኪንግስ ሆቴል አጠገብ ግደይ ገ/ሂዎት ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ከግዢና አቅርቦት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ጨረታው በ03/05/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር ) በታሸገ ፖስታ ከፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 5(አምስት) ቀናት ውስጥ ዉል ተፈራርሞ ክፍያዉን በመክፈል መኪኖችን መረከብ  አለባቸዉ፡፡
 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 7. ተጫረቾች መኪኖችን ለማየት ቃሊቲ ከዉሀ ልማት 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘዉ ናሺናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሺን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋብሪካ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

አድራሻ: አዲስ አበባ ሳር ቤት አካባቢ ኪንግ ሆቴል አጠገብ ግደይ ገ/ሂዎት ህንፃ 4ተኛ ፎቅ፤ ስልክ ቁጥር 0118225392/ 0991202020