ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 07/24/2022
- Phone Number : 0114426000
- Source : Reporter
- Closing Date : 08/13/2022
Description
የ ጨ ረ ታ ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ. | የተሽከርካሪ ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
1 | ሱዙኪ አልቶ አውቶሞቢል | ቁጥር | 5 |
2 | ሱዙኪ ዲዛየር አውቶሞቢል | ቁጥር | 1 |
3 | ፕራዶ ቶዮታ | ቁጥር | 1 |
4 | ኤክስትራ ካቢን ፒክ አፕ ቶዮታ | ቁጥር | 1 |
5 | ክሬን ዳብል አክስል (ቶይንግ ክሬን) | ቁጥር | 2 |
- ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባና የታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ከላይ በተ.ቁ 1- 5 ለተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች የሚገልፀውን የጨረታ ሠነድ ከሐምሌ19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (3ኛ ፎቅ) በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ በሰፈረው የገንዘብ መጠን መሠረት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ)/ የባንክ ጋራንቲ ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ እና ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 2፡45 ሰዓት ድረስ 3ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 06 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ጎተራ ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ 3ኛ ፎቅ
የስልክ ቁጥር ፡- 011 442 60 00 አዲስ አበባ፡፡