ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የክበብ አገልግሎት ግዥ ጨረታ

-ኢንሹራንስ-ኩባንያ-አ.ማ-Logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 01/10/2021
 • Phone Number : 0114426000
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/22/2021

Description

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.

NILE INSURANCE COMPANY S.C.

የክበብ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ለዋናው መ/ቤት ሠራተኞች በኩባንያው ሕንፃ እና የካፍቴሪያ ቁሳቁስ፣ የክበብ አገልግሎት አሟልቶ የሚያቀርብ ድርጅት/ግለሰብ በጨረታ በማወዳደር አሸናፊ ከሆነው ጋር ተገቢውን ውል በመፈፀም ለሠራተኞቹ የክበብ አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ኩባንያው ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መሠረት መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

 1. 1. ስለክበብ አገልግሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሥራ ሰዓት የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
 2. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) በናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ ሥም ከመጫረቻ ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት፡፡
 3. ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሠ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተ.ዕ.ታ. እና የታክስ ከፋይነት ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የተሟላ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዋጋ ማቅረቢያ እና ደጋፊ የስራ ልምድ ማስረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ እስከ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 3ኛ ፎቅ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው በዕለቱ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡15 ሰዓት በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ዋና መ/ቤት (ጎተራ)

ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (3ኛ ፎቅ)

የመ. ሣ. ቁ. 12836

የስልክ ቁጥር 0114-42-60-00

Send me an email when this category has been updated